ድንገተኛ አደጋዎች በአዲስ አበባ ምን ይመስላሉ?
በከተማዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች ምክንት 56 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል
በደረሱ 392 አደጋዎች ምክንያት 670 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት እንደወደመም ተገልጿል
ድንገተኛ አደጋዎች በአዲስ አበባ ምን ይመስላሉ?
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 392 አደጋዎች ደርሰዋል የተባለ ሲሆን በነዚህ አደጋዎች ምክንያትም የ56 ሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል፡፡
በአደጋዎቹ ሳቢያ ከሰው ህይወት ባለፈ 670 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ወድመዋል የተባለ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች 85 ሰዎችን እና 11 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረትን ከመውደም እንደታደጉ ተገልጿል፡፡
ጎርፍ፣ ክፍቱን በተተው ጉድጓዶች ውስጥ መግባት፣ እሳት አደጋ እና ሌሎች ያልታወቁ አደጋዎች ደግሞ በከተማዋ ከደረሱ አደጋዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡