የፊሊፒንሱ ፕሬዝዳንት በመጪው ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ
ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ቀደም ሲል ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለላቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ዱቴርቴ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት በምትወዳደረው ልጃቸው ሳራ ዱቴርቴ ምክንያት ራሳቸውን ከምርጫው አግለዋል
የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ በፈረንጆቹ 2022 በሚካሄደው ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ።
ሮድሪጎ ዱቴርቴ በምርጫው የማይሳተፉት ልጃቸው የምርጫው ተወዳዳሪ በመሀኗ ከእርሷ ጋር ላለመፎካከር እንደሆነ ገልጸዋል።
የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ እንደገለጹት ዱቴርቴ ቀደም ሲል ለምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር አቅደው ነበር። ይሁንና ልጃቸው ሳራ ዱቴርቴ ለፊሊፒንስ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ስለምትወዳደር ፕሬዝዳንቱ ላለመወዳደር ወስነዋል ተብሏል።
የዱቴርቴ ቃል አቀባይ እንዳሉት ፕሬዝዳንቱ እና ልጃቸው እርስ በእርስ አይፎካከሩም። የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደማይችሉ የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ያግዳቸዋል።
ይሁንና ለምክትል ፕሬዝዳንት እንዳይወዳደሩ የሚከለክል ሕግ ባለመኖሩ ፕሬዝዳንት ዱዱቴርቴ ለመወዳደር ዕቅድ ይዘው ነበር።
ፓርቲያቸው ፓርቲዶ ዴሞክራቲኮ ፊሊፒኖ ላካስ ባያን (ፒዲፒ ላባን) ለምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ደግፍቷቸው እንደነበር ተገልጿል።
የሀገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለቀጣይ ዓመት ምርጫ የሚያቀርቧቸውን ዕጩዎች የሚያቀርቡበት የመጨረሻ ቀን ዛሬ እንደሆነ ተገልጿል።
የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ቀደም ሲል ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለላቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል።
ይሁን እንጅ ምክትል ፕሬዝዳንት ለመሆን ፉክክር ውስጥ እንደሚገቡ ገልጸው ነበር። ምንም እንኳን ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደማይችሉ በሕግ ቢቀመጥም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እና ለኮንግረንስ አሊያም ከንቲባነት ለመወዳደር የሚከለክላቸው ነገር የለም ተብሏል።