ፖለቲካ
የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ራሳቸውን ከፖለቲካ እንደሚያገሉ አስታወቁ
ሆኖም ሳራ የተባለች ሴት ልጃቸው በቀጣዩ ዓመት ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደምትወዳደር ታውቋል
ዱቴርቴ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ይዘው የነበረውን እቅድ ስለመሰረዛቸውም አስታውቀዋል
የፊሊፒንሱ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ በጡረታ ከፖለቲካ እንደሚገለሉ አስታወቁ፡፡
ዱቴርቴ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ይዘው የነበረውን እቅድ ስለመሰረዛቸውም አስታውቀዋል፡፡
ይህን ውጥናቸውን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር የህዝብን ፍላጎት አድምጫለሁ ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በፊሊፒንስ ህገ መንግስት መሰረት አንድ ሰው ለአንድ የስልጣን ዘመን ማለትም ለ6 ዓመታት ብቻ ነው ስልጣን ላይ የሚቆየው፡፡
ዱቴርቴ ይህን በሚቃረን መልኩ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ማስታወቃቸው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡
በተቃዋሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንም ቀስቅሷል፡፡ ይህን ተከትሎም ነው ውጥናቸውን መሰረዛቸውን ያስታወቁት፡፡
ሆኖም የዳቫዎ ከተማ ከንቲባ የሆነችው ልጃቸው ሳራ ዱቴርቴ ካርፒዮ በቀጣዩ ዓመት ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደምትወዳደር አስታውቀዋል፡፡
በቅርቡ ከቦክስ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን ያስታወቀው ፓኪያዮ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደርፓኪያዮ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡