ባዕድ ነገርን ከማር እና ቅቤ ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ የነበሩ 72 ግለሶች በፖሊስ ተያዙ
ባዕድ ነገርን ከማር እና ቅቤ ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ የነበሩ 72 ግለሶች ታህሳስ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ግለሰቦቹ እያንዳንዱ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን 1ሺ 196 ማዳበሪያ ማር እና 80 ባልዲ ማር እንዲሁም ለጠጅ የተዘጋጀ 10 በርሜል ማር፣ አንድ ደርዘን ወይም 10 ፍሬ ነጭ ቀለም ያለው የማር መቀመሚያ፣ ግማሽ ማዳበሪያ ጨው ፣ ጨው መሰል የውሃ ማጣሪያ ባዕድ ነገር፣ 45 ኪሎ ግራም ስኳር፣ እና
እያንዳንዱ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን 228 ማዳበሪያ፣እያንዳንዱ 24 ኪሎ ግራም የሚመዝን 14 ባልዲ እና 4 ካርቶን ቅቤ፣96 ባልዲ ቪክተቢል (የቅቤ መቀመሚያ)፣ 35 ባልዲ ቦቼ የሚረጋ ዘይት ቀላቅለው ሲሸጡ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ማርና ቅቤው ንጽህናው ባልተጠበቀ ስፍራ ተቀምጦ እንደነበርም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡
የኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ቡድን ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር ባካሄደው የጋራ ኦፕሬሽንም ታህሳስ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ጀምሯል፡፡
ግለሰቦቹ በሰበታ፣ፉሪ እና በ9 የተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች መያዛቸውንም ነው፣ ህብረተሰቡ በበዓል የግብይት ቀናት ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ያሳሰበው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡