ጋርዲዮላ “ማንቸስተር ሲቲ ቶተንሃምን ማሸነፍ ካልቻለ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሊያጣ ይችላል” አሉ
የቶትንሃም አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ጨዋታውን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልጸዋል
ፕሪምየር ሊጉን አርሰናል በ86 ነጥብ ሲመራ አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ሲቲ በ85 ነጥብ 2ኛ ላይ ተቀምጧል
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “ማንቸስተር ሲቲ ቶተንሃምን ማሸነፍ ካልቻለ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሊያጣ ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በነገው እለት የአንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቶትንሃምን ከማቸስተር ሲቲ እንደሚያገናኝ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።
በቶትንሃም ሜዳ በሚደረገው ጨዋታ ላይ ማንቸስተር ሲቲ ማሸነፍ ከቻለ ለዋንጫው የሚያደርገውን ግስጋሴ የበለጠ ያጠናክረዋል።
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ዙሪያ በተጫዋቾቻቸው ላይ የሚያደርጉትን ጫና ከፍ አድርጓል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት፤ ቡድናቸው በነገው አለት ከቶተንሀም ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ከማሸነፍ ውጪ ምንም ምርጫ እንደሌው ገልፀዋል።
ሲቲ ሻምፒየን መሆኑን ለማረጋገጥ ከፍተኛውን ነጥብ መሰብሰብ የግድ ይለናል ብለዋል አሰልጣን ፔፕ ጋርዲዮላ።
ማንቸስተር ሲቲን በሜዳቸው የሚያስተናግደው የቶትንሃም አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ጨዋታውን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልጸዋል።
አሰልጣኙ በንግግራቸውም “ለማንችስተር ሲቲ ክብር አለን ነገር ግን ከሲቲ ያለንን ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን” ብለዋል።
ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የአንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒየን የሚሆንውን ክለብ ለመለየት እስከ ውድድሩ ዓመት ማጠናቀቂ መጠበቅ የግድ ሆኗል።
ትናንት በ37ኛ ሳምንት በማቸስተር ዩናትድ እና በአርሰናል መካከል በኦልትራፎድ የተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በአርሰናል አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም አርሰናል የሊጉ መሪ መሆን ችሏል።
ይህንን ተከትሎም ይህንን ተከትሎም አርሰናል በ86 ነጥብ የፕሪምየር ሊጉን የመሪነት ስፍራ ሲረከብ፤ ቀሪ አንድ ጨዋታ ያለው ማንቸስተር ሲቲ በ85 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።