በዘንድሮው የረመዳን ጾም ወር ረጅም እና አጭር ሰዓት የሚጾምባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የረመዳን ጾም መቼ ይጀመራል?
የዘንድሮው የኢድ በዓል ሚያዝያ መግቢያ ቀናት ላይ እንደሚከበር ይጠበቃል
በዘንድሮው የረመዳን ጾም ወር ረጅም እና አጭር ሰዓታት የሚጾምባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የረመዳን ጾም ወር የፊታችን መጋቢት ላይ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
ለአንድ ወር በሚቆየው ይህ ልዩ የጾም እና ጸሎት ወቅት መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢምሬት ጠፈር ሳይንስ ማህበረሰብ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የዘንድሮው የረመዳን ጾምን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ የት አካባቢ ረጅም የጾም ሰዓት እንዲሁም በየሀገራቱ የሚኖሩ የጾም ሰዓታትን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት የተወሰኑ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ከተሞች በ24 ሰዓታት ውስጥ እስከ 18 ሰዓታት ያህል ሊጾሙ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
ግሪንላንድ፣ ሄልሲንኪ፣ ግላስኮው፣ ኦታዋ፣ ለንደን፣ ፓሪስ፣ ሮም፣ ዙሪክ እና ማድሪድ ቀኑ ረጅም በመሆኑ ምክንያት ሙስሊሞች ከ15 እስከ 18 ሰዓታት ሊጾሙ ይችላሉ ብሏል፡፡
በረመዳን የጾም ወቅት ከምግብ ጠረጴዛዎ እንዳይጠፉ የሚመከሩ ምግቦች የትኞቹ ናቸው?
ቺሊ፣ ኒውዝላንድ፣ ኬንያ፣ ፓኪስታን፣ ሕንድ እና ኢንዶኔዢያ ያሉ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ደግሞ ከ12 እስከ 14 ሰዓታ ሊጾሙ እንደሚችሉም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡
እንደ ሳውዲ አረቢያ እና ግብጽ ባሉ የመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ሀገራት ደግሞ ከ13 እስከ 15 ሰዓታት ሊጾም እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የልዩ ጾም፣ ጸሎት እና የመረዳዳት ወር የሚባለው ረመዳን በየዓመቱ በየ10 ቀን እና ከዛ በላይ በሆኑ ልዩነት ቀናት ውስጥ የሚመጣ ሲሆን የዓምናው ረመዳን ወር ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ማብቃቱ ይታወሳል፡፡