አመጋገብን ማስተካከል ሰውነታችን በጾሙ እንዳይዳከም ለማድረግ እንደሚያግዝ ይነገራል
ቅዱሱ የረመዳን የጾም ወር ዛሬ መጀመሩ በይፋ ተነግሯል፡፡ የጾም ወሩ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ተግባራት የሚከበር ሲሆን መጾም መጸለዩ የተለመደ ነው፡፡ ይህን ተከትሎም በወራቱ ከማዕዱ የሚቀርቡ የምግብ ዐይነቶች በጾም የተዳከመውን ሰውነት ማበርታት የሚችሉ እንዲሆኑ ይመከራል፡፡
አል ዐይን አማርኛም በረመዳን የጾም ወቅት ከምግብ ጠረጴዛዎ እንዳይጠፉ የሚመከሩ ምግቦች የትኞቹ ናቸው? በሚል ተከታዩን ዝርዝር አዘጋጅቷል፡፡
ቴምር
ቴምር መብላት ለሰውነት ሃይል ብክነት ማካካሻ እና የስርዓተ ፆታ ስርዓትን ለመቆጣጠር ይረዳል
መጠጦች
እንደ ውሃ፣ ወተት ወይም የተፈጥሮ የፍራፍሬ ጭማቂ ያሉ መጠጦች ማዘውተር ከጾም በኋላ ሰውነታችን አስፈላጊውን እርጥበት እንዲያገኝ ያግዛል
ፕሮቲን
ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች በዚህ ወቅት መጠቀሙ ይመከራል፡፡ የተቀቀለ ዶሮን ከተጠበሰ አትክልት ጋር ወይም የተጠበሰ አሳ፣ ቡናማ ሩዝ እና የተጠበሱ አትክልት በረመዳን ወቅት ከሚመከሩ ምግቦች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ሾርባ
ሾርባ ለመጠቀም ቀላል፣ ለሆድ ምቹ፣ለፆመኛ ጉልበት የሚሰጥ እና ሰውነት ያጣውን ውሃ የሚተካ ነው ይባላል፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ከምስር፣ ገብስ፣ አትክልት የዶሮ መረቅ እና ጥራጥሬ የሚዘጋጅ ሾርባ በጾም ወቀት ተመራጭ ነው፡፡
አትክልቶች
በዚህ ወቅት ከጠረጴዛዎ እንዳይጠፉ ከሚመከሩ የምግብ ዐይነቶች መካከል አትክልቶች ተቀዳሚ ናቸው፡፡ 5 ያህል የአትክልት ዓይነቶችን ያካተተ የሰላጣ ምግብ ከጠረጴዛዎ ቢኖር ይመረጣል፡፡ እንደ ኤግፕላንት፣ የታሸጉ ቃሪያዎች እና የወይን ቅጠሎች በጾም ወቅት በጠጴዛዎ እንዲኖሩ የሚመከሩ ምግቦች ናቸው፡፡
ካርቦሃይድሬትስ
በጾም እና በጸሎት የሚደክመው ሰውነት ይበረታ ዘንድ ጉልበት የሚሆን ካርቦሃይድሬት ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህም እንጀራ፣ ዳቦ ወይም ሩዝን የመሳሰሉ ምግቦችን ማዘውተሩ ጠቃሚ ነው፡፡
ፍራፍሬዎች
በረመዳን ወቅት በቫይታሚን እና በማዕድናት የበለጸጉ የተሻለ የንጥረ ምግብ ይዞታ ያላቸውን አቮካዶ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ አናናስ፣ ማንጎ እና ሌሎችንም መሰል ፍራፍሬዎች ማዘውተር ቢችሉ ይመከራል፡፡