ውፍረትና ሱስን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያች ለመካንነት በመንስዔነት የተቀመጡ ሲሆን፤ መፍትሄዎችም እንደሚከተለው ቀርበዋል
በስነ ተዋልዶ ጤና ዘርፍ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች ከዘር ፍሬ መጠን መቀንስ ጋር በተያያዘ በወንዶች ላይ የሚከሰት መካንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱን ይጠቁማሉ።
ለሰው ልጅ መጸነስ ዋነኛ መሰረት የሆነው የወንዶች የዘር ፍሬ ወይም ስፐርም ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ መሆኑን ሳይንቲስቶች መግለጻው ይታወሳል።
አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው (ወንድ) በአማካኝ በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ከ20 እስከ 150 ሚሊዮን ሚሊ ሊትር የዘርፍሬ የሚረጭ ሲሆን ለእርግዝና ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ሚሊ ሊትር የዘር ፍሬ በቂ እንደሆነ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ።
ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ያለው የወንድ የዘር ፍሬ መጠን በየጊዜው እየቀነሰ መምጣቱን ዩሮ ኒውስ ተመራማሪዎችን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ከ50 ዓመታት በፊት በአንድ ሚሊ ሊትር የወንድ የዘር ፍሬ ፈሳሽ ውስጥ 101 ሚሊየን የዘር ፍሬዎች የነበሩ ሲሆን፤ አሁን ላይ ወደ 49 ሚሊየን ዝቅማለቱንም ያነሳሉ።
የወንድ የዘር ፍሬ መጠን እንዲቀንስ የሚያደርጉ ምክንያቶች
1. ከመጠን በላይ ውፍረት
ወንዶች ከመጠን በላይ ሲወፍሩ የዘር ፍሬን የሚያመርቱ ህዋሶች (ሴሎች) ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ወንዶች ውስጥ 39 በመቶው ወፍራሞች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ውስጥ 11 በመቶ ከልክ በላይ ለሆነ የሰውነት ውፍረት የተጋለጡ ናቸው።
ይህም ባለፉት 50 ዓመታተ ውስጥ የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን እየቀነሰ እንዲሄድ ምክንያት እንደሆነ ያሳያል ተብሏል።
2. ሱስ
በዓለም ዙሪያ ለአልኮል መጠጥ፣ ሲጋራ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና እንዲሁም አደንዛዣ የሆኑ መድሃኒቶች ሱሶች የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በርካታ እንደሆነ ይነገራል።
ከላይ የተዘረዘሩትን ጨምሮ ሌሎችም ለሱስ የሚዳርጉ ነገሮች የወንዶች የዘር ፍሬ ላይ ጉዳት ከሚያስከትሉት ውስጥ ዋነኞቹ እንደሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች እታውቀዋል።
3. በጾታዊ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች
በጾታዊ ግንኙነት ወቅት በባክቴሪያ አማካኝነት የሚተላለፉ እንደ ጨብጥ ያሉ በሽታዎች በወንድ የዘር ፍሬ መተላለፊያ ላይ በሚያስከትሉት እብጠት አማካኝነት የዘር ፍሬ ሴል ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
4. ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር ጭናችን ላይ ማስቀመጥ
የወንድ የዘር ፍሬ ከመደበኛው የሰውነታችን ሙቀት በአንድ ወይ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ባነሰ ሙቀት ውስጥ መቆየት እንዳለበት የሚነገር ቢሆንም፤ ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ ግን ወንዶች ኮምፒውተር በጭናቸው ላይ አድርገው ከመጠቀማቸው የተነሳ የዘር ፍሬያቸውን ለአደጋ እያጋለጡ ነው ተብሏል።
ኮምፒውተሩ በሚሞቅበት ጊዜ ሙቀቱ ደ ሰውነታችን በመሸጋገር የወንድ የዘር ፍሬን ከመጠን በላይ ሙቀት አግኝቱ ወደ ማብሰል ሊያደርስ ይችላል የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች ሰዉነታችንን ለሙቀት የሚዳርጉ ነገሮችም የዘር ፍሬ ከሚጎዱ ነገሮች መካከል ይገኛሉ ተብሏል።
መፍትሄው ምንድነ ነው?
ልጆች እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ወንዶች የዘር ፍሬያቸው ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ለማስቀረት የአኗኗር ዘይቤያቸውን መቀየር ለይ ቢያተኩሩ መልከም ነው ተብሏል።
የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣
አልኮል መጠጣን ማቆም፣ ሲጋራን ጨምሮ ሌሎች አድንዛዥ እጾችን መጠቀም ማቆምን የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ።