ሩሲያ ባለፉት ቀናት ውስጥ 500 የዩክሬን ወታደሮችን ገደልኩ አለች
ከምዕራባዊያን ለዩክሬን የተለገሱ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟንም ሩሲያ አክላለች
ሩሲያ በሞስኮ የኖርቄይ ዲፕሎማትንም ማባረሯን አስታውቃለች
ሩሲያ ባለፉት ቀናት ውስጥ 500 የዩክሬን ወታደሮችን ገደልኩ አለች፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት 162ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ጦርነቱ ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ዓለም አቀፋዊ ሆኗል።
የሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት ቀናት በተካሄደው ጦርነት 500 የዩክሬን ወታደሮች መግደሉን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ አክሎም ከአሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን አውድሜያለሁም ብሏል።
የሩሲያ ጦር በዶንቴስክ እና ካርኪቭ አካባቢዎች ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ በርካታ የዩክሬን እና ቅጥረኛ ወታደሮች ይዞታዎችን እና የጦር ማዘዣዎችን ማውደሙንም አስታውቋል።
እንዲሁም ከረጅም እና አጭር ርቀት ሚሳኤል መሳሪያዎች፣ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ መጋዝኖችን እና ሌሎች ወታደራዊ ስፍራዎችን የሩሲያ አየር ሀይል መምታቱን አርቲ ዘግቧል።
የሩሲያ ጦር 390 የዩክሬን የጦር አውሮፕላኖች ፣ 1506 ድሮኖች፣ 354 ጸረ አውሮፕላን ሚሲኤሎች እና ከ 11 ሺህ በላይ የጦር ታንኮች፣ ልዩ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ ጸረ ሮኬት መሳሪያዎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ማውደሙን ዘገባው አክሏል።
የዩክሬን መንግስት በሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር መግለጫ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
በተያያዘ ዜና ሩሲያ ከሰሞኑ አንድ የኖርዌይ ዲፕሎማት በአንድ መዝናኛ ስፍራ ገብታ በተናገረችው ጸረ ሩሲያ ንግግር ምክንያት ሞስኮን ለቃ እንድትወጣ መወሰኗን አስታውቃለች።