ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ የሩሲያ “ዋነኛ ስጋት” ነች ሲሉ ፈረጁ
ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በሩሲያ እና በምእራባውያን መካከል ያለው ፍጥጫ አይሏል
ፕሬዝዳንቱ የሩሲያን የባህር ኃይል ሰፊ ስትራቴጂካዊ አላማዎችን የያዘ ባለ55 ገጽ ሪፎርም ፈርመዋል
ሩሲያ ፕሬዝደንት ቫላድሚር ፑቲን አሜሪካን ዋነኛ የሩሲያ ጠላት አድርገው ፈረጁ፡፡
ፕሬዝደንት ፑቲን ይህን ያሉት በሩሲያ በሴንት ፒተርስበርግ በተከበረው እና ታሪካዊ ነው በተባለው የባህር ቀን ላይ ነው፡፡
ባለፈው ቅዳሜ አዲስ የባህር ኃይል መተዳደሪያ ላይ ፊርማቸውን ያስቀመጡት ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ ዋነኛ የሩሲያ ተቀናቃኝ አድርገው አስቀምጠዋል፡፡ በአዲሱ የባህር ኃይል መተዳደሪያ በአርክቲክ እና በጥቁር ባህር ሊኖር የሚችለው የሩሲያ እቅድ መነደፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በታላቁ ቄሳር ፒተር በተመሰረተችው የቀድሞዋ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሴንት ፒተርስበርግ በተከበረው የሩሲያ የባህር ኃይል ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ሩሲያን ታላቅ የባህር ሃይል እንዲኖራት የያደረጉትን ፒተርን አመስግነዋል፡፡
ፑቲን የባህር ሃይሉን ከጎበኙ በኋላ አጭር ንግግር ያደረጉት ሩሲያ ልዩ የሆነችው የዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳኤሎች በማሳየት ሩሲያ ወታደራዊ አቅም እንዳላት አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ንግግር ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ የሩሲያን የባህር ኃይል ሰፊ ስትራቴጂካዊ አላማዎችን የያዘ ባለ55 ገጽ ሪፎርም ፈርመዋል፡፡
ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በሩሲያ እና በምእራባውያን መካከል ያለው ፍጥጫ አይሏል፡፡
ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ያወጀችው።
ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።
በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል። የዶምባስ ግዛትን ነጻ የማውጣት የወሰነቸው ሩሲያ አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡