ሩሲያ፤ ጆ ባይደን ጉብኝታቸውን “ሪያድን ጸረ-ሞስኮ ለማድረግ እንደማይጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ” አለች
የክሬምሊን ቃል አቀባይ፤ በዓለም የነዳጅ አምራቾች ማዕቀፍ ውስጥ ከሳዑዲ ጋር ለምናደረግገው ትብብር ከፍተኛ ዋጋ እንሰጣለን ብለዋል
ጆ ባይደን መካከለኛው ምስራቅን ለመጎብኝት ጉዟቸውን በዛሬው እለት ጀምረዋል
ሩሲያ፤ ጆ ባይደን በጉብኝታቸው የሳዑዲ ሰዎች ለአሜሪካ የሚያቀርቡት የነዳጅ ምርታቸውን እንዲያሳድጉ ለማሳመን እንደሚጥሩ ሁሉ “ሪያድን ጸረ-ሞስኮ ለማድረግ እንደማይጠቀሙበት ተስፋ ደርጋለሁ” አለች፡፡
የኋይት ሀውስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ሰኞ ዕለት እንደተናገሩት፤ ባይደን በዚህ ሳምንት የሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ ከባህረ ሰላጤው መሪዎች ጋር ሲገናኙ ከየነዳጅ ላኪ ሀገሮች ድርጅት /OPEC / አባል ሀገራት ከፍተኛ የነዳጅ ምርት ለማግኘት በሚቻልበት ጉዳይ የሚመክሩ ይሆናል፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንዳሉት ሩሲያ ከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል ሁለተኛዋ የነዳጅ ዘይት ላኪ እና የአለም ትልቁ የተፈጥሮ ጋዝ ላኪ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በ ኦፔክ + ቡድን የዓለም መሪ የነዳጅ ዘይት አምራቾች ማዕቀፍ ውስጥ ለምታደርገው ትብብር ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለች ብለዋል ።
"እኛ በኦፔክ + ስምምነቶች ማዕቀፍ ውስጥ ነን፣ እና እንደ ሳዑዲ አረቢያ ካሉ ዋና አጋሮች ጋር ልንሰራው የምንችለውን ስራ በጣም እናደንቃለን" ሲሉም ለጋዜጠኞች መናገራቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
"ከሪያድ ጋር ያለንን ግንኙነት በጣም እናደንቃለን እናም በሪያድ እና በሌሎች የዓለም ኃያላን መካከል ያለው ግንኙነት በምንም መልኩ በኛ ተቃራኒ እንደማይቆም በእርግጠኝነት ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉም አክለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
ሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በሩሲያ ላይ የሚጣለው ማዕቀብ መቀጠሉ በዓለም ላይ ባሉ ሸማቾች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እያስከተ መሆኑ በቅረቡ ምዕራባውያንን ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡
ጆ ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ ለሚያደርጉት ጉብኝት ጉዞ በዛሬው እለት ጀምረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን ጉብኝታቸውን ዛሬ በእስራኤል የሚጀምሩ ሲሆን፤ በመቀጠልም ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያቀኑ ይሆናል።
ባይደን በእስራኤል ቆይታቸው ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር የሚወያዩ ሲሆን፤ ዌስት ባንክን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን በእስራኤል የሚኖራቸውን ቆይታ ሲያገባድዱ ከሳዑዲ አረቢያ እና በባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ከሚገኙ የግብጽ፣ ኢራቅ እና ዮርዳኖስ መሪዎች ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏዋል፡፡