ኃላፊው የታሰረው በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሶ ነው
የሩሲያ የሃይፐርሶኒክ ፕሮግራም ኃላፊን በሀገር ክህደት ወንጀል ክስ አስራለች።
ሮይተርስ የሩሲያውን ታስ የዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘገበው የሩሲያ የጸጥታ ባለስልጣናት በሀገር ክህደት ወንጀል የተከሰሰውን የሃይፐርሶኒክ ፕሮግራም ኃላፊ ይዘው አስረዋል።
ኃይፐርሶኒክ መሳሪያዎች ከድምጽ አምስት አሰጥፍ ፍጥነት ያላቸው ሲሆን ሌሎች እንደ ኪንሃል ያሉ ሚሳየሎች ደግሞ ከጽምጽ 10 እጥፍ ፍጥነት አላቸው።
ሁለት አይነት የኃይፐርሶናክ ሚሳየሎች አሉ፤ በከፍተኛ ሞተር የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሚሳየል የሚተኮሱና ኢላማ የሚመቱ ናቸው።
ሩሲያ፣ ቻይና እና አሜሪካ በጣም ዘመናዊ የሚባል ሱፐርሶኒክ ሚሳየል ያላቸው ሌሎች ሀገራት ማለትም ጃፖን፣ጀርመን፣ህንድና አውስትራሊያን ጨምሮ ኃይፐርሶኒክ ሚሳየል የታጠቁ ናቸው።
ሩሲያ ከፈረንጆቹ 1980ዎቹ ጀምሮ ጥረት ስታደርግ የቆየች ቢሆንም አሜሪካ ከጸረ ባሊስቲክ ሚሳየል ስምምነት በፈረንጆቹ 2002 ከወጣች እና የአሜሪካ የሚሳየል መከላከያ ወደ አውሮፖ ከተላከ በኋላ ግን ሩሲያ ሚሳየል የማልማት ጥረቷን ከፍ አድርጋዋለች።
ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ከምእራባውያን ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብታለች። አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ማእቀብ ሁሉ ጥለውባታል።
ሩሲም በአንጻሩ በምስራቅ እና ደቡባዊ ዩክሬን ያለውን ዘመቻ ቀጥላለች።