የቡድን 20 ሀገራት ያልተጠበቀውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ጉዳይ ዙሪያ እየመከሩ ነው
የቡድን 20 ሀገራት ያልተጠበቀውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ጉዳይ ዙሪያ እየመከሩ ነው
የቡድን20 አባል ሀገራት ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳኡዲ አረቢያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡ በበይነ መረብ አማካኝነት በሳኡዲ አረቢያ የሚካሄደውን ስብሰባ በሳኡዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን ቢንአብዱላዚዝ መሪነት በሪያድ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ስብሰባው ኮሮና ቫይረስ አለምአቀፍ አደጋ ሆኖ ባለበት ወቅት በአለም ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ በሚያሳድሩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፤ መረጋጋትና ብልጽግና ለማምጣት አላማ ያደረገ ነው፡፡ ስብሰባው በአረብ ሀገር መሪነት ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
ቡድን20 ከአውሮፓ ህብረት በተጨማሪ 19 ሀገራትን ያካተተ ሲሆን ለአለምአቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር ዋና ፎረም በመሆን ትልቅ ኢኮኖሚ ያላቸውንና በፍጥነት እያደጉ ያሉ ሀገራትን ለማካተት የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡
ቡድን20 2/3ኛውን የአለም ህዝብ የሚያጠቃልል ሲሆን ሀገራቱ 77 በመቶ የሆነው የንግድ ልውውጥ ይሸፍናሉ፡፡ የቡድን 20 ሀገራት ያልተጠበቀውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ እንደሚመክሩ ተገልጿል፡፡