ሳኡዲ አረቢያ ሁሉንም መስጊዶች ዘጋች
ሳኡዲ አረቢያ ሁሉንም መስጊዶች ዘጋች
ሳኡዲ አረቢያ በትናንትናው እለት እንዳስታወቀችው ልዩ በተባለው እርምጃዋ ሁሉም መስጊዶች ለመደበኛም ሆነ ለጁምኣ ጸሎት ክፍት እንደማይሆኑ ማስታወቋን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሀገሪቱ የቡድን 20 ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ላይ ልዩ የሆነ የኦንላይን ስብሰባ እንደሚያካሂዱም አስታውቃለች፡፡
በሀገሪቱ አስካሁን 171 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የቡድን 20 ሀገራትን በሊቀመንበርነት የምትመራው ሳኡዲ አርቢያ የተባበረ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለማስቀመጥና ህዝብን ለመከላከል ልዩ ስብሰባ እንደሚኖር አስታውቃለች፡፡
የአሜሪካ አጋር የሆነችው ሀገሪቱ ብዙ የቫይረሱ ተጠቂዎችን አስተናግዳለች፤ አብዛኞቹ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በመካከለኛው ምስራቅ የበሽታው ማእከል ወደ ሆነችው ጎረቤት ኢራን በሚያደርጉት ጉዞ የተከሰተ ነው ተብሏል፡፡
ከቻይና ውሀን ግዛት የተነሳው ኮሮና ቫይረስ እስካሁን 144 ሀገራትን አዳርሷል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ወረርሽን ብሎ ካወጀ ሳምንታትን አስቆጥሯል፡፡