ህንድ የሩፒ-ሪያል ንግድን ተቋማዊ ለማድረግ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር መምከሯን ገልጻለች
የህንድ እና የሳኡዲ አረቢያ መንግስታት በራሳቸው ገንዘብ መገበያየት ለመጀመር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ህንድ ይፋ አድርጋለች።
የህንድ መገበያያ ገንዘብ ሪፒ ሲሰኝ የሳኡዲ አረቢያ ደግሞ ሪያል ይባላል።
ህንድ ባለፈው ሰኞ እንዳስታወቀችው የሩፒ-ሪያል ንግድን ተቋማዊ ለማድረግ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር መምከሯን ገልጻለች።
ሁለቱ ሀገራት በህንድ የነዳጅ ማጣሪያ ማቋቋም እና የፔትሮሊየም ማከማቻን መሰራት ጨምሮ በሌሎች የጋራ ኘሮጀክቶች ላይ እንደሚተባበሩ መረጋገጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከእሲያ በኢኮኖሚ ግዝፈቷ ሶስተኛ የሆነችው ህንድ አለምአቀፍ የንግድ ልውውጦችን በህንድ ሩፒ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች ነው፤ ኢኮኖሚዋም ወደ ውጭ በመነገድ ወይም ኤክፖርት በማድረግ ላይ ትኩረት እንደምታደርግ ገልጻለች።
በፈረንጆቹ ሚያዚያ እስከ ሐምሌ ደረስ ህንድ ከሳኡዲ አረቢያ ያስገባችው በ93 በመቶ ሲያድግ ኤክፖርት ያደረገችው ደግሞ በ22 በመቶ ወደ 3ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር አድጓል።
የሳኡዲ ንጉስ መሀመድ ቢን ሳልማን በፈረንጆቹ 2019 ህንድን በጎበኙበት ወቅት በህንድ 100 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት እናደርገለን ማለታቸው ይታወሳል።