ንጉሱ ከግብጽ አቻቻው ጋር በመገናኘት በዩክሬኑ ጦርነት እና ጆ ባይደን በሳኡዲ ለሚያደርጉት ጉብኝት በሚደረገው ዝግጅት ላይ መክራሉ ተብሏል
የሳኡዲ አረቢያው ልኡል በሚያካሄዱት ቀጣዊ የጉብኝት መርሃግብር በፈረንጆቹ ሰኔ 20 ግብጽን እንደሚጎበኙ ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የሳውዲው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ያቀዱት የግበጽ ጉብኝት በጆርዳን እና በቱርክ የሚደረጉት ቀጣና ጠጉብኝት አካል መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡
ልኡል መሀመድ ከግብፁ ፕሬዝዳንትን አብደል ፋታህ አል ሲሲን በማግኘት የዩክሬን ጦርነት በአካባቢው ባመጣው ተጽእኖ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሚቀጥለው ወር ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለሚያደርጉት ጉብኝት ዝግጅት ላይ እንደሚመክሩ ምንጮቹ ተናግረዋል።
የሳኡዲ ባለስልጣናት የልዑል መሀመድን ጉብኝት አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም ብሏል ዘገባው።
ሳዑዲ አረቢያ የግብፅ የቅርብ አጋር ስትሆን ሲሲ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ለካይሮ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች።
የፖርትፎሊዮ ባለሀብቶች ከግብፅ ገንዘብ ሲሰበስቡ እና በዩክሬን ጦርነት መጀመሪያ ላይ መንግስት የሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱ ሳዑዲ አረቢያ 5 ቢሊዮን ዶላር በግብፅ ማዕከላዊ ባንክ ማስቀጣ ይታወሳል፡፡
የግብፅ መንግስት ከሳዑዲ ሉዓላዊ የሀብት ፈንድ ጋር በመተባበር 10 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ያስችላል ብሏል።