የአቡ ዳቢ ልዑል እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሼክ መሀመድ ቢን ዘይድ ለስራ ጉብኝት ፓኪስታን ገቡ
የአቡ ዳቢ ልዑል እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሼክ መሀመድ ቢን ዘይድ አል ነህያን ለስራ ጉብኝት ወደ ፓኪስታን ያመሩት ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው፡፡
ልዑሉ ኢስላማባድ ሲደርሱ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ፓኪስታን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ላለፉት አስርት ዓመታት ጠንካራ ፈርጀ ብዙ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የአሁኑ የልዑሉ ጉብኝት ይሄን ግንኙነት ማጠናከርን ያለመ ነው፡፡
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በአረብ-ኤሲያ ግንኙነትም ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታመናል፡፡
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የፓኪስታን ኮሚዩኒቲ አባላት ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ፓኪስታናዊያን ለሁለቱ ሀገራት እድገትና ብልጽግና ከሚጫወቱት ሚና በተጨማሪ የሀገራቱን ትብብር እና ትስስር ለማጠናከርም ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡
ልዑሉ ትናንት በሩሲያ አለማቀፍ ቴሌቪዥን-RT በተሰበሰበ ድምጽ፣ በ 2019 ለሰላም እና አለማቀፍ ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ምርጥ የአረብ መሪ ተብለው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡