የሐረር ሸዋል ኢድ በዓል (በፎቶ)
ሸዋል ኢድ የኢድ አልፈጥር በዓል ከተከበረ አንድ ሳምንት አልፎ በሀረሪ ብሄረሰብ ዘንድ ይከበራል
በዓሉ ምሽት ለሚከበረበት የጀጎል አካባቢ ድምቀት ነው
የሐረር ሸዋል ኢድ በዓል ምሽቱን በሐረር ጀጎል ግንብ ተከብሯል።
ሸዋል ኢድ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል አንድ ሳምንት አልፎ በሀረሪ ብሄረሰብ ዘንድ የሚከበር ነው።
በሐረር በየዓመቱ በኢድ አልፈጥር በዓል ሳምንት የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር ትናንት ምክሽት በድምቀት ተካሂዷል።
ሸዋል ኢድ በሀረር በጀጎል ዙርያ ካሉ አምስት በሮች በሁለቱ ማለትም በየረር በር እና ፈላና በር በየዓመቱ የሚከበር በዓል ነው።
ሸዋል ዒድ በሀረሪ ወጣቶች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ዓመታዊ በዓል ነው።
በዓሉ በተለይ ወጣቶች ውሀ አጣጭ የሚመረርጡበት፣ የተፈላለጉ የሚተጫጩበት መሆኑ ትዕይንቱን ያማረ ያደርገዋል።
የሀረሪ ክልል ዓመታዊው የሸዋል ዒድ በዓል በዓለም አቀፉ የቅርስ ጥበቃ ተቋም / ዩኔስኮ እውቅና እንዲያገኝ እንቅቀስቃሴዎች እያደረገ ነው