ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዛሬው እለት በ375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ጀምሯል
ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ትልቅ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በዛሬው እለት ኃይል ማመንጨት ጀመረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ግድቡ እየተገነባ በሚገኝበት ጉባ ተገኝተው የግድቡን አንድ ተርባይን ሃይል የማመንጨት ስራ በይፋ አስጀምሯል።
የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት ከ84 በመቶ በላይ ደርሷል።
ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት አቅም አለው፤ በዓመትም 15 ሺህ 760 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል እንደሚመነጭ ተነገሯል።
ለግድቡ ግንባታ እስካሁን ከ163 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።