1443ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በፎቶ
ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል
በበዓሉ ላይ የጎረቤት ሀገራት የእስልምና ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
1443ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም የእስልምና የእምነት አባቶች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ከጎሮቤት አገራት የወጡ እንግዶች ፣ ዳያስፖራዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፤ “ወደ ልማት ልንመለስ ይገባል፤ የንጹሃን ደም አይፍሰስ፣ ሰዎች አይፈናቀሉ፣ አንዱ አንዱን አይዝረፍ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።