ድምጻዊው በሙዚቃው ዘርፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ የጅማ እና የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ሰጥተውታል
አንጋፋው ድምጻሚ አሊ ቢራ ህይወቱ ማለፉን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታውቋል፡፡
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው ድምጻዊ አሊ ቢራ በአዳማ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ሲታከም መቆየቱን እና በዛሬ ምሽት ህይወቱ ማለፉን አስታውቋል፡፡
ቢሮው በድምጻዊው ህልፈተ ሕይወት ማዘኑን ገልጿ፡፡
በድምጻዊ ሞት ሃዘናቸውን በትዊተር ገጻቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከግማሽ ምእተ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ለሰብአዊ መብት ድምጽ ሆኗል ብለዋል፡፡
የድምጻ አሊ ቢራ ስራዎች”ዛሬ የሚሰሙ እና ነገ የሚናፈቁ ሳይሆን ትናንት የነበሩ፣ ዛሬ እና ነገ የሚሰሙ“ ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ድምጻዊ አሊ ቢራ በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ትልቅ ቦታ ያላቸው እና ዝናን ያተረፈ ነው፡፡ አሊ ቢራ 1954 ዓ.ም አፈፍረንቀሎ የተሰኘውን የሙዚቃ ባንድ ከመሰረቱ አንዱ ሲሆን የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃን በማስተዋወቅ ስራ እንደሰራ ይነገራል፡፡
ድምጻዊ አሊ ቢራ ከኦሮምኛ በተጨማሪ በሶማሊኛ፣ በአፋርኛ፡ በሐረሪ፣ በአማርኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች በርካታ ዘፈኖችን ተጫውቷል፡፡
የጅማ እና የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች ድምጻዊው በሙዚቃው ዘርፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት በመስጠት አውቅና መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ድምጻዊ አሊ ቢራ በግንቦት 1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ነው የተወለደው፡፡