የሶማሊያው ጠ/ሚ ሞሀመድ ሁሴን የሶማሊያ ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርን ከስራ አባረሩ
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጀነራል በሽር ሞሀመድ ጃማንን አዲስ የደህንነት ሹም አድርገው ሾሟል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሁሉም የመንግስት ተቋማት ከአዲሱ የስለላ ተቋም ዳይሬክተር ጋር ተባብረው እንዲሠሩ” አዘዋል
የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒሰትር ሞሀመድ ሁሴን /ሮብሊ/ የሀገሪቱ የደህንነት መስርያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ፋሃድ ያሲን ሀጂ ጣሂርን ከስልጣን አባረሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በፋሃድ ያሲን ምትክ ከወታደር ቤት የተገኙት ጀነራል በሽር ሞሀመድ ጃማን ጊዝያዊ የደህንነት ሹም አድርገው መሾማቸው ተወስቷል፡፡
ጠቅላይ ሚነሲትሩ እርምጃ ለመውሰድ የተገደዱት የደህንነት ሹሙ የሚሰጣቸውን ትእዛዝ ወደ ጎን በመተው የግትርነት ባህርይ ይስተዋልባቸው ስለነበር ነውም ተብለዋል፡፡
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “ከሰኔ 26 ጀምሮ ከእይታ የተሰወረችውና የደህንነት መስርያ ቤቱ ባልደረባ የነበረችው ኢክራም ታህሊል ያለችበት ቦታና ሁኔታ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደረጉ ቢያዙም የደህንነት ሹሙ ትእዛዛቸው ሳያከብሩ መቅረታቸው” ለእርምጃው ምክንያት መሆኑ ተገልጸዋል፡፡
ባለፈው ሐሙስ የደኅንነት ተቋሙ የኢክራምን ሞት በአልሸባብ በኩል ቢያውቅም ኃላፊነት የሚወስደውን አካል ከመግለጽ ተቆጥቦ ነበር፡፡
“በፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት፣ የኢክራም ወደ አልሻባብ እጅ መውደቅና መገደል እና የስለላ አካውንት አለመተማመን” የመሳሰሉም ሌሎች ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በደህንነት ሹሙ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ያስገደድዋቸው ምክንያቶች ናቸው፡፡
በዚህ “የኢክራም ጉዳይ” የተነሳም የጠቅላይ ሚነሲትሩ እና የደህንነት ሹሙ ግንኙነት በጊዜ ሂደት እየሻከረ መጥተዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በተሰጠ ድንጋጌ መሠረት አምስት ነገሮችን የያዘ ውሳኔም ተላልፈዋል፡፡
የሚኒስትሩ ድንጋጌ “የሶማሊያ የስለላና የብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተሩ ያሲን መታሰራቸውንና እና ጄኔራል በሽር መሐመድ ጃማ የኤጀንሲው አዲስ ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን” የሚያካትት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዋጁ መሠረት“ሁሉም የመንግስት ተቋማት ከአዲሱ የስለላ ተቋም ዳይሬክተር ጋር ተባብረው እንዲሠሩ” ሲሉም አዘዋል።
ጠ/ሚኒሰትር ሮበሊ ፡ ፋሃድ ያሲን ከሰኞ ጀምሮ ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ ኃላፊነታቸው ለአዲሱ የስለላ ኃላፊ እንዲያስረክቡና እንዲያስተላልፉም ትእዛዝ አስተላለፍዋል።
ሮቤሊ “ወታደራዊ አቃቤ ህጉ በጠፋችው የስለላ መኮንን ኢክራም ተህሊል ፋራህ ጉዳይ ላይ ግልፅ እና ጥልቅ ምርመራ አጠናቋል ፣ የምርመራውን ውጤት ፤በኢክራም አፈና እና ግድያ ውስጥ የተሳተፈውን ሁሉ በሀገሪቱ ኦፊሴላዊ ፍርድ ቤቶች ፊት እያቀረበ ነው” ብሏል።
የጠቅላይ ሚኒሰትሩ እርምጃ ሶማሊያ በከፍተኛ የፖለቲካ ትኩሳት ወቅት ባለችብት ወቅት የተወሰደ መሆኑ ግን በበርካቶች ዘንዳ ስጋት ሳይጭር አልቀረም፡፡