በደቡብ አፍሪካ 45 ሰዎች ከሞቱበት የመኪና አደጋ አንድ 8 ዓመት ልጅ ብቻ በህይወት ተረፈቸ
በደቡብ አፍሪካ 46 ሰዎችን አሳፈሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ከድልድይ ላይ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት አልፏል
በአውቶብሱ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ለፋሲካ በዓል ከቦትስዋና ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ የነበሩ ናቸው
በደቡብ አፍሪካ ትናንት ምሽት በደረሰ እና 45 ሰዎች ከሞቱበት የመኪና አደጋ አንድ 8 ዓመት ልጅ ብቻ በህይወት መትፈሯ ተነገረ።
አደጋው የደረሰው 46 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ድልድይ ጥሶ 50 ሜትር ርቀት ያለው ገደል ውስጥ በመገልበጡ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በአደጋውም በአውቶብሱ ውስጥ ተሳፍረው ከነበሩት 46 ሰዎች መካከል የ45 ሰዎች ህይወት ያለሰ ፊሆን፤ አንዲት የ8 ዓመት ሴት ልጅ ብቻ በህይወት ተርፋለች።
ከአደገው በህይወት የተረፈችው የ8 ዓመቷ ሴት ልጅ ወደ ሆስፒታል መወሰዷን ነው የተገለጸው።
አደጋው የተከሰተውም በደቡብ አፍሪካ ሰሜን ምስራቋ ሊምፖፖ ግዛት ሲሆን፤ ከቁጥጥር ውጪ የሆነው አውቶብስ የድልድዩን የብረት መከላከያ አጥር በመጣስ ገደል ውስጥ ከወደቀ በኋላ በእሳት በመያያዙ መሆኑን ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።
በአውቶብሱ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ለፋሲካ በዓል ኃይማታዊ ስነ ስርዓት ከቦትስዋና ዋና ከተማ ጋሮኒ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሞሪያ ሲጓዙ የነበሩ ናቸው።
የደቡብ አፍሪካ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሲንድዋይዝ ቺኩንግ አደጋው የደረሰበትን ቦታ ሄደው የተመለከቱ ሲሆን፤ በአደጋው የተሰማቸውን ሀዘንም ገልጸዋል።
የደቡብ አፍሪካ መንግስት አስከሬኖቹን ወደ ሀገራቸው እንደሚለሱ እንደሚያደርግ እና የአደጋውን መንስኤ ሙሉ ምርመራ እንደሚያደርግም ትንስፖርት ሚኒስትሯ ተግናረዋል።
የደቡብ አፍሪካፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቀደም ብለው ነባስተላፉት የትንሳኤ በዓል መልእክት ለዜጎቻቸው “ደህንነቱ የተጠበቀ ፋሲካ ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ እንዲያደርጉ” አሳስበዋል።