የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆችው ኒውዮርክ የመስመጥ አደጋ እንዳንዣበበባት የከርሰ ምድር ባለሙያዎች ተናግረዋል
በዘመናዊ ከተማ ታሪክ የብዙ የዓለማችን ምሳሌ የሆነችው ኒዮርክ ከተማ የመስመጥ አደጋ እንዳንዣበበባት የከርሰ ምድር ጥናት ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ከሆነ በኒዮርክ ከተማ በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ቶን በላይ ጠጣር የግንባታ ግብዓቶች፣ ብረቶች እና መስታዋት ግንባታ ይካሄዳል።
ይህ ከፍተኛ ክብደት መጠን ያላቸው ምርቶች አጠቃላይ መሬቱ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።
በዚህ ምክንያትም ኒዮርክ ከተማ ልትሰጥም እና አካባቢው በውሀ ሊሞላ እንደሚችል ባለሙያቆቹ አስጠንቅቀዋል ተብሏል።
የዓለማችን የዲፕሎማሲ መዲና የምትባለው ኒዮርክ ተመድን ጨምሮ የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዋና ከተማ ነች።
በተለይም ማንሀተን፣ ብሩክሊን እና ኪዊንስ የተሰኙት የኒዮርክ ከተማ አካባቢዎች ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ቁሳቁሶች መሬት ላይ አሉ ተብሏል።
በአጠቃላይ ኒዮርክ ከተማ በየዓመቱ እስከ አራት ሜትር ድረስ ወደ ውስጥ እየሰመጠች መሆኑን በሮድ አይስላንድ ዩንቨርስቲ የከርሰ ምድር ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ከተማዋ ከባህር ወለል በላይ ያላት ርቀት ከ50 ዓመት ከነበራት ጋር ሲነጻጸር በ20 ሴንቲ ሜትር ጭማሪ አሳይቷል።
በዚህ ምክንያት ኒዮርክ ከተማ የመሬት መንሸራተት፣ ውሀ መጥለቅለቅ እና መብረቅ አደጋዎች ያላት ተጋላጭነት መጨመሩ ተገልጿል።
የከተማዋ አስተዳድር በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላሮችን በማውጣት የባህር ውሀ መከላከያ አጥር፣ የፍሳሽ ማስወገጃ እና ሌሎች የአደጋ መቀነሻ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም ሰዎች ከወዲሁ በአደጋዎች መሞት ጀምረዋል።
ለአብነትም በፈረንጆቹ 2012 እና 2021 ላይ ባጋጠመ የውሀ መጥለቀለቅ አደጋ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።