ደቡብ ሱዳን ግዛቶቿን ከ32 ወደ 10 ዝቅ አደረገች
“ዛሬ የወሰነው ውሳኔ የሚያም ነው፤ ነገር ግን ሰላም የሚያመጣ ከሆነ አስፈላጊ ነው”- ፕሬዘዳንት ኪር
ደቡብ ሱዳን የግዛቶቿን ቁጥር ከ32 ወደ 10 ዝቅ አደረገች
ደቡብ ሱዳን የግዛቶቿን ቁጥር ከ32 ወደ 10 ዝቅ አደረገች
የደቡብ ሱዳን መንግስት ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ደቡብ ሱዳን የግዛቶቿን ቁጥር ከ32 ወደ 10 ዝቅ ማድረጓን ያስታወቁ ሲሆን፣ ይህም ቆሞ የነበረውን የሰላም ሂደት የሚያስጀምርና ለአንድነት መንግስት ምስረታ እድል እንደሚሰጥ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
“ዛሬ የወሰነው ውሳኔ የሚያም ነው፤ ነገር ግን ሰላም የሚያመጣ ከሆነ አስፈላጊ ነው” ብለዋል ፕሬዘዳንት ኪር በመግለጫቸው፡፡
ፕሬዘዳንቱ የሀገሪቱ ተቃዋሚዎችም ተመሳሳይ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ እጠብቃለሁ ብለዋል፡፡ኢጋድ ደቡብ ሱዳን እስከ ዛሬ ድረስ ቅዳሜ ምንያህል ግዛቶች ሊኖሯት እንደሚችል እንድታሳውቅ ቀነ ገደብ ሰጥቷት ነበር፡፡
በደቡብ ሱዳን ምንያህል ግዛት ይኑር የሚለውና የተለያዩ ተዋጊ ኃይሎችን ወደመደበኛ ሰራዊት የማዋሀድ ጉዳይ፣ በሳልቫ ኪርና በሪክ ማቻር መካከል ያለው አለመግባባት እንዲቀጥልና ለሰላም ሂደቱ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡
“በጥቅሉ ፕሬዛዳንቱ ሀገሪቱን ወደ 10 ግዛት ዝቅ ማደረጋቸውን እንቀበላን” ያሉት ደግሞ የሪክ ማቻር ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ማናዋ ፒተር ናቸው፡፡
ቃል አቀባዩ ይህ የሰጥቶ መቀበል ውሳኔ ነው፤ ፕሬዘዳንቱ የወሰዱትን ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ እናደንቃለን ብለዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ከሱድን ተገንጥላ እ.ኤ.አ በ2011 ሀገር ከሆነች በኋላ ለአምስት አመታት የቆየ የእርስበእርስ ጦርነት ተቀስቅሶ ምናልባትም ከሩዋንዳ የዘርማተፋት በኋላ አስከፊ የሚባል ስደተኞችን መፍጠሩ ይታወሳል፡፡
በአሜሪካና በተባበሩት መንግስተት ድርጅት ጫና ምክንያት ኪርና ማቻር እ.ኤ.ኤ. በ2018 የሰላም ስምምነት ፈርምው ነበር፡፡