በጉዳዩ ላይ ከስዊድን ባለስልጣናት በይፋ እንዳልተነገረው የኖሮዎይ ውጭ ሚኒስቴሩ ገልጿል
የስዊድን ስፔስ ኮርፕ(ኤስኤስሲ) ከኢስራንጅ የስፔስ ማዕከል የተኮሰው ሮኬት 15 ኪ.ሜ ኖርዋይ ውስጥ ከተጓዘ በኋላ ተቀላሽቶ ተከስክሷል።
በሙከራው ሮኬቱ 250 ኪ.ሜ በመጓዝ የመሬት ስበት ዜሮ በሆነበት እርቀት ላይ ደርሶ ነበር።
ኤስኤስሲ ኃላፊ ፊልፕ ኦህልሰን እንደገለጹት አንድ ሺ ሜትር ከፍታ ባለው ተራራማ ቦታ አርፏል።
ኃላፊው እንዲህ አይነት ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል እና ሁነቱን ለስዊድን እና ለኖርዋይ መንግስት ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።
ኤስኤስሲ ሮኬቱ ለምን በተሳሳተ አቅጣጫ እንደሄደ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል ብሏል።
የኖርዎይን ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ በኖርዎይ ድንበር በኩል የሚደረጉ እውቅና የሌላቸው እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ እንደሚከታተሏቸው ገልጸዋል።
የድንበር ጥሰት ሲያገጥም ኃላፊነት ያለባቸው የኖርዎይ የውጭ ጉዳይን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካለት ማሳወቅ እንዳለባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
በጉዳዩ ላይ ከስዊድን ባለስልጣናት በይፋ እንዳልተነገረው የኖሮዎይ ውጭ ሚኒስቴሩ ገልጿል።