ለአጭር ጊዜ ታስራ የነበረችው የስዊድኗ የአየር ንብረት አክቲቪት ተንበርግ ተፈታች
በሰሜን ዌስት ፌሊያ የሚገኘው መንደር የከሰል ማእድን ማውጫ ቦታን ለማስፋፋት እየፈረሰ ነው
ግሬታ ተንበርግ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባደረገችው ዘመቻ አለምአቀፍ እውቅና ተችሯታል
ለአጭር ጊዜ በጀርመን ታስራ የነበረችው የአየር ንብረት አክቲቪስት ግሬታ ተንበርግ ተፈትታለች።
የከስል ማእድን ለማውጣት የሚደረገውን የቤት ማፍረስ ከሌሎች አክቲቪስቶች ጋር በመቃወሟ ብትታሰርም ፖሊስ ማንነቷን ካጣራ በኋላ እንደለቀቃት ሮይተርስ ዘግቧል።
ተንበርግ በፖሊስ የተያዘችው ፖሊስ የከሰል ማእድን የሚወጣቀት የመጨረሻው ጫፍ ላይ እያስጠነቀቃት በመሄዷ ነው።
በሰሜን ዌስት ፌሊያ የሚገኘው መንደር የከሰል ማእድን ማውጫ ቦታን ለማስፋፋት እየፈረሰ ነው።
የጀርመን መንግስት ከማእድን አውጭው ድርጅት ጋር በደረሰው ስምምነት መንደሮቹ እንዲፈርሱ መደረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ተንበርግን ጨምሮ አክቲቪስቶቹ ጀርመን የከስል ማእድን ማውጣቷን ትታ በታዳሽ ኃይል ላይ መስራት አለባት ብለዋል።
ግሬታ ተንበርግ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባደረገችው ዘመቻ አለም አቀፍ እውቅ ተችሯታል።