ታሊባን የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን መውጣቱን ተከትሎ ነበር ሀገሪቱን ተቆጣጥሮ ማስተዳደር የጀመረው
አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ ያለው ታሊባን "የቀጣናው እና አለምአቀፍ" ሀገራት ይፋዋ እውቅና እንዲሰጡት ጥሪ አቅርቧል። የታሊባን አስተዳደር ይህን ንግግር ያሰማው በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድ ሃይማኖተኞችን እና የጎሳ መሪዎችን ሰብስቦ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ነገርግን ታሊባን አለምአቀፋ ማህበረሰብ የሚፈልገውን የሴቶች ትምህርት ቤትን መክፈት ጨሞሮ ሌሎች ጥያቄዎች ላይ ያሳየው ለውጥ የለም ተብሏል።
የአፍጋኒስታን ኢኮኖሚ ምእራባውያን በጣሉት ማእቀብ ምክንያት ክፉኛ ተጎድቷል፤ ማእቀቡ የተጣለው ታሊባን በተለይም በሴቶች ላይ የመብት ጥሰት እፈጸመ ነው በሚል ነው።
"ቀጣናዊ እና አለምአቀፍ ሀገራት በተለይም ሙስሊም ሀገራት ለአፍጋኒስታን እስላማዊ መንግስት እውቅና እንዲሰጡን እንጠይቃለን። ማእቦች ይነሱ፤እገዳ የተጣለቀት ገንዘብ ይለቀቅ" በማለት የታሊባን ቡድን ለተሳታፊው ንግግር አሰምቷል።
የቡድኑ መሪ 4ሺ ለሚሆኑ ሰዎች ባሰማው ንግግር ታሊባን ድለ አድርጓል፤ነጻ ወጥታችኋል እንኳን ደስአላችሁ የሚል ንግግር አሰምቷል።
የታሊባን አማጺ ቡድን በአፍጋኒስታን ለአመታት የተንቀሳቀሰ ሲሆን የአሜሪካን ጦር መውጣት ተከትሎ ሀገሪቱን ተቆጣጥሮ እያስተዳደረ ነው።