ቴስላ ኩባንያ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የተሸጡ መኪኖች እንዲመለሱ ጠየቀ
ኩባንያው መኪኖቹ እንዲመለሱ የጠየቀው የምርት ጥራት መጓደል አጋጥሟል በሚል ነው
ድርጅቱ ከ2020 ጀምሮ የተመረቱ አራት አይነት ሞዴሎች የሶፍትዌር ችግር አለባቸው ብሏል
ቴስላ ኩባንያ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የተሸጡ መኪኖች እንዲመለሱ ጠየቀ፡፡
የዓለማችን ቀዳሚ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ የሆነው ቴስላ ከ1 ነጥብ 68 ሚሊዮን በላይ ምርቶቹ ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በኢለን መስክ የተመሰረተው ይህ ኩባንያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማምረት የሚታወቅ ሲሆን በደንበኞቹ እጅ የሚገኙ ምርቶቹ እንዲመለሱ ጠይቋል፡፡
ዩሮ ኒውስ ኩባንያውን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2024 ባሉት ዓመታት ውስጥ የተመረቱ የተወሰኑ የድርጅቱ ምርቶች እክል አጋጥሟቸዋል፡፡
በተለይም ሞዴል ኤስ፣ ሞዴል ኤክስ እንዲሁም በቻይና የተመረቱት ሞዴል 3 እና ዋይ ምርቶች ላይ የምርት አክል በማጋጠሙ ችግሮች እንዲስተካከሉ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
አሜሪካዊያን ከኤሌክትሪክ መኪኖች ፊታቸውን ለምን አዞሩ?
የኩባንያው የሽያጭ ክፍል እንዳሳወቀው ምርቶቹ ያጋጠማቸው የሶፍትዌር ችግር ሲሆን ባሉበት ሆነው ችግራቸውን መፍታት ይቻላል ሲል አሳውቋል፡፡
ከዚህ በፊት መሰል የሶፍትዌር ችግሮች አጋጥመው እንደማይውቁ የገለጸው ኩባንያው መሰል ችግር ያለባቸው መኪኖች በመነዳት ለይ እያሉ የኋላ በራቸው መከፈት እና ሌሎች ክፍሎች መከፈት ያጋጥማል ተብሏል፡፡
ቴስላ ኩባንያ ብዙ ሸማቾች ባለባት ቻይና ከተሰማራ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መሰረታቸውን ቤጂንግ ያደረጉ ተመሳሳይ ኩባንያዎች ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ቴስላ ኩባንያ ትርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እንደመጣበት የኩባንያው ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በአንጻሩ የቻይና ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች በቻይና እና በመላው ዓለም ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ ሲመጣ ትርፋቸውም በማሻቀብ ለይ እንደሚገኝ በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡
የአውሮፓ እና አሜሪካ ኩባንያዎች የቻይናን ተጽዕኖ ለመመከት በሚል ግብር ከመጨመር ጀምሮ ሌሎች እርምጃዎችን በመውሰድ ለይ ይገኛሉ፡፡