ተሽከርካሪው ያለጭነት ብቻ 360 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው መኪናው በሰዓት እስከ 64 ኪሎ ሜትር ይጓዛል
ቡልጋሪያ በመጫን አቅሙ ከዓለም አንደኛ የሆነ ተሸከርካሪ ሰራች፡፡
የቀድሞዋ የሶቪየት ህብረት አንድ አካል የሆነችው ቡልጋሪያ ተሸከርካሪዎችን በማምረት ጥሩ ልምድ ያላት ሀገር ነች፡፡
ለሩሲያ ባላት ቅርበት ከምዕራባዊያን ጋር የሻከረ ግንኙነት ያላት ቡልጋሪያ የዓለምን ክብረ ወሰን የሰበረ በግዝፈቱ የመጀመሪያ ነው የጠባለ ተሽከርካሪ ማምረቷን አስታውቃለች፡፡
ልዩ መለያው ቤልዜዜድ-75710 የተሰኘው ይህ የዓለማችን ግዙፍ ተሽከርካሪ 503 ሺህ ኪሎ ግራም ይመዝናል ተብሏል፡፡
ተሽከርካሪው በተለይም በማዕድን ማውጣት ስራ ለተሰማሩ ኩባንያዎች ዋነኛ ተመራጭ ነው የተባለ ሲሆን በዚህ ዘርፍ በዓለም ተመራጭ ለሆኑት ካተርፒላር፣ ሌብሄር እና ቡሴረስ ኩባያዎች ጥሩ ዜና እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡
ተሽከርካሪው ማዕከሉን በቤላሩሷ ዞዲኖ ከተማ ባደረገው ቤልኤዜድ በተሰኘው ኩባንያ የተሰራ ሲሆን በመጫን አቅሙ እና በመጠኑ የዓለማችን ግዙፉ ተሽከርካሪ ተብሏል፡፡
ይህ ተሸከርካሪ ብቻውን እቃ ከመጫኑ በፊት 360 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን አንዱ ጎማ ብቻውን 5 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡
20 ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ተሽከርካሪ እያንዳንዳቸው 2 ሺህ 300 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ሀይል ሰጪ ሲሊንደሮች ሲኖሩት በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላልም ተብሏል፡፡
ኩባንያው አሁን ላይ ሶስት ቤልኤዜድ-75710 ሞዴል ተሸከርካሪዎችን ያመረተ ሲሆን ሶስቱም ተሽከርካሪዎች በሩሲያ መገዛታቸው ተገልጿል፡፡