ሶስት አሜሪካውያን በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢምባሲ ሰራተኞች የፍርድ ሂደቱን እየተከታተሉት ነበር ብሏል
አሜሪካውያኑ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሚና ነበራቸው ተብለው የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው 37 ግለሰቦች ውስጥ ሆነዋል
ሶስት አሜሪካውያን በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው።
በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ(ዲአርሲ) ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ ሶስት አሜሪካው በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።
አሜሪካውያኑ ባለፈው ግንቦት ወር በተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሚና ነበራቸው ተብለው በወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው 37 ግለሰቦች ውስጥ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ግንቦት ወር የታጠቁ ኃይሎች መሪያቸው መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ኮንጓዊ ፖለቲካኛ ክርስቲያን ማላንጋ በጸጥታ ኃይሎች ከመገደሉ በፊት ለአጭር ጊዜ የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ወርረው ነበር።
ከጓደኛው ታይለር ቶምሰን ጋር የተከሰሰው የማላንጋ ልጅ ማርሴል ማላንጋም ከተከሰሱት አሜራካውያን ውስጥ ይገኝበታል።ሁለቱም እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ነው።
ሶስተኛ የተከሰሰው አሜሪካዊ ቤንጃሚን ዛልማን ፖሉን የክርስቲያን ማላንጋ የንግድ ሸሪክ ነው። ሶስቱም አሜሪካውያን በሴራ፣ በሽብር እና በሌሎች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በቴለቪዥን በተላለፈ የፍርድ ሂደት የሞት ቅጣት ተላልፎባቸዋል።
ማላንጋ አባቱ በድርጊቱ ካልተሳተፈ እንደሚገለው ዝቶበት እንደነበር ለፍርድ ቤት ገልጾ ነበር። ኮንጎን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጎብኘት የመጣው ለረጅም አመታት ያላየው አባቱ ጋብዞት እንደሆነም ገልጿል።
አሜሪካውያኑ የከሸፈውን መፈንቀለ መንግስት ተከትሎ ክስ ከመሰረተባቸው የእንግሊዝ፣ የካናዳ፣ የቤልጄየም እና የኮንጎ ዜጎችን ጨምሮ ከ50 ግለሰቦች ውስጥ ናቸው። 37 ተከሳሾች የሞት ቅጣት ተላልፎባቸዋል።
ፍርዱ ከኪንሻሳ ከተማ ዳርቻ ከሚገኘው የንዶላ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ በተተከለ በአዳራሽ ውስጥ ተነቧል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቴው ሚለር የኢምባሲ ሰራተኞች የፍርድ ሂደቱን እየተከታተሉት መሆኑን እና አዳዲስ ሀነቶቸን መከታተላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ በኮንጎ ያለው የህግ ሂደት ፍርደኞች ይግባኝ የሚጠይቁበት አሰራር እንዳለ ተረድተናል ብሏል።