የደቡብ ኮሪያ መንግስት የሰሜን ኮሪያን መንግስት ዩራኒየም የመጨመር እቅድ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል
ሰሜን ኮሪያ የዩራኒየም ማበልጸጊያ ጣቢያዋን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳየች።
ሰሜን ኮሪያ ለኑክሌር የጦር መሳሪያ ግብአት የሚል ዩራኒየም የምታበለጽግበትን ጣቢያ ምን እንደሚመስል ለመጀመሪያ ጊዜ በፎቶ አሳይታለች።
ፎቶው ቀደም ሲሉ የሀገሪቱን የኑክሌር ኃይል በከፍተኛ ቁጥር እንደሚጨምሩ የዛቱት መሪው ኪም ጆንግ ኡን ቦታውን ሲቃኙ ያሳያል። የሰሜን ኮሪያ የመንግስት ሚዲያ የሆነው ኮሪያን ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲ(ኬሲኤንኤ) ባለፈው አርብ እለት ኪም የዩራኒየም ምርት እንዲጨምር ጥሪ ማቅረባቸውን ዘግቧል።
ዩራነየም ማበልጸግ ለኑክሌር የጦር መሳሪያ ምርት በጣም አስፈላጊ ነው።
ፎቶው ኪም በዩራኒየም ማበልጸጊያ ጣቢያው ውስጥ ሲዘዋወሩ እና ከወታደራዊ ባለስልጣናት ጋር ሲወያዩም የሚያሳይ ነው። ይህ ፎቶ ይፋ የሆነው በኮሪያ ባህረሰላጤ ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት ነው።
"ኪም አጠቃላይ የምርት ሂደቱን በዩራኒየም ማበልጸጊያ ጣቢያው ውስጥ በሚገኘው የመቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ በመዘዋወር አይተዋል" ያለው ጣቢያ "ጥንካሬ" ይሰማኛል ማለታቸውንም አክሎ ገልጿል።
የደቡብ ኮሪያ መንግስት የሰሜን ኮሪያን መንግስት ዩራኒየም የመጨመር እቅድ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል።
ሰሜን ኮሪያ ኪም ጉብኝቱን መቼ እንዳደረጉት እና የትኛውን ጣቢያ እንጎበኙ ግልጽ አላደረገችም። ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ሰሜን ኮሪያ በግልጽ ከሚታወቀው የዮንግብዮን በተጨማሪ አንድ በሚስጥር የምትመራው የዩራኒየም ማበልጸጊያ ጣቢያ እንዳላት የረጅም ጊዜ ጥርጣሬ አላቸው።
የደቡብ ኮሪያ የውህደት ሚኒስቴር ጣቢያውን ይፋ ያደረገችውን ሰሜን ኮሪያን አውጎዞ፣ህገወጥ የሆኑ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ስምሪቶች በርካታ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ህጎችን የሚጥሱ ናቸው ሲልም አክሏል።
ሚኒስቴር ከሰሜን ኮሪያ በኩል ሊኖር የሚችል የኑክሌር ጦር መሳሪያ ትንኮሳ ጠንካራ ምላሽ ይሰጠዋል ብለዋል።
ሰሜን ኮሪያ ምን ያህል የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳላት ባይታወቅም፣ አንድ በቅርቡ የወጣ ግምት ግን ቁጥሩን 50 አድርጎታል።
ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና አጋሮቿን የደህንነት ስጋቷ አድርጋ ፈርጃለች።