ብዙ አጫሾች ያሉባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ከሌሴቶ አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 26 በመቶ ያህሉ ሲጋራ አጫሾች ናቸው
ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካም በአንጻራዊነት ብዙ ዜጎች ሲጋራ ከሚያጨሱ ሀገራት መካከል ናቸው
ብዙ አጫሾች ያሉባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ሲጋራ ማጨስ በዓለማችን ሰዎችን ለጽኑ ህመሞች ከሚዳርጉ እና እንዲሞቱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ዋነኛው ነው፡፡
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ለልብ ህመም፣ ደም ግፊት፣ ካንሰር እና ሌሎች ገዳይ በሽታዎች ያጋልጣሉ፡፡
በዓለም ላይ በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የሲጋራ አጫሾች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝብ ሲጋራ ያጨሳልም ተብሏል፡፡
ወደ አፍሪካ ስንመጣ ሌሴቶ፣ ሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ በአንጻራዊነት ብዙ ዜጎች ሲጋራ የሚጨስባቸው ሀገራት ናቸው፡፡