ኒውዝላንድ ሲጋራ እንዳይጨስ የሚከለክለውን ህግ ልትሽር ነው
ይህ ህግ ከፈረንጆቹ ጥር 1፣2009 ወዲህ ለተወለደ ሲጋራ እንዳይሸጥ ይከለክላል
ሀገሪቱን እየመራ ያለው ሴንተር ራይት ካኦሊሽን በላቦር ፖርቲ በሚመራው የቀድሞው መንግስት የጸደቀውን ህግ ለመሻር ማቀዱ ተገልጿል
ኒውዝላንድ ሲጋራ እንዳይጨስ የሚከለክለውን ህግ ልትሽር ነው።
የጤና ባለሙያዎች እንደተናገሩት ኒውዝላንድ የሚቀጥለው ትውልድ ሲጋራ እንዳያጨስ የሚከለክለውን ህግ ለመሻር ማቀዷ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል እና ማጨስን ለመቀነስ የሚደረገውን አለምአቀፍ ጥረት አደጋ ውስጥ የሚያስገባ ነው።
ሀገሪቱን እየመራ ያለው ሴንተር ራይት ካኦሊሽን በላቦር ፖርቲ በሚመራው የቀድሞው መንግስት የጸደቀውን ህግ እንደሚሽረው መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ህግ ከፈረንጆቹ ጥር 1፣2009 ወዲህ ለተወለደ ሲጋራ እንዳይሸጥ፣ በሚጨሰው ቶባኮ ውስጥ ያለው የኒኮቲን መጠን እንዲቀነስ እና የቶባኮ ቸርቻሪዎች ቁጥር ከ90 በመቶ በላይ ዝቅ እንዲል የሚያደርግ ነው።
የኒውዝላንድ የቶባኮ ወይም ሲጋራ ህግ በአለም ላይ ካሉት ህጎች ጥብቆ ተደርጎ ይወሰዳል። የሚቀጥለው ትውልድ እንዳያጨስ የሚለው የክልከላ ሀሳብ በእንግሊዝም ቀርቦ ነበር።
"ይህ ለህብረተሰብ ጤና ከፍተኛ ችግር ሲሆን በሰው ህይወት ትርፍ ለሚያካብቱት ለቶባኩ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ድል ነው" ሲሉ በኒውዝላንድ የጤና ጥምረት አኦተራ ሰብሳቢ ቦይድ ስዊንበርን ተናግረዋል።
ጥምረቱ ህጉ በጤናው ዘርፉ በ20 አመታት ሊወጣ የሚችለውን 1.3 ቢሊዮን ዶላር ማዳን እና የሞት ምጥነትን መቀነስ የሚያስችል መሆኑን የአካዳሚ ጥናትን ጠቅሶ አመልክቷል።
በሎንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የቶባኮ እና አልኮል ሪሰርች ቡድን ውስጥ ዋና ተመራማሪ የሆኑት ሳራህ ጃክሰን ውሳኔ የሌላ ሀገራትን እቅድ ላይ አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።
ተመራማሪዋ እንደገለጹት የኒውዝላንድ ውሳኔ መቀልበስ የእንግሊዝ ፖሊሲ አውጭዎች እቅዱን እንዲያጤኑት ሊያርጋቸው ይችላል።