ህወሓት ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታወቀ
በአፍሪካ ሀብረት ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ የነበረው ህወሓት በህብረቱ ጥላ ስር በሚካሄደው ድርድር እንደሚሳተፍ ገልጿል
የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱ በድጋሚ ከመቀስቀሱ በፊት ያለቅደመ ሁኔታ እንደሚደራደር መግለጹ ይታወሳል
ህወሐት ከመንግስት ጋር ለሚያደረግው የሰላም ንግግር ጌታቸው ረዳን እና ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በድጋሚ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛው ቦታ ከህወሓት ጋር እንደሚደራደር መግለጹም ይታወሳል፡፡
ህወሐት ዛሬ ማምሻው በትግራይ የውጭ ግንኙነት ጸ/ቤቱ በኩል ባወጣው መግለጫ የተሰየመው ተዳራዳሪ ቡድን ወደፊት በሚደረገው ድርድር “የትግራይን መንግስት” የሚወከል ስልጣን ተሰጥቶታለል ብለዋል፡፡
ህወሓት የተሰየመው ተደራዳሪ ቡድን በአጭር ጊዜ ወደ ድርድር ይገባል ብሏል፡፡
በአፍሪካ ሀብረት ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ የነበረው ህወሓት በህብረቱ ጥላ ስር በሚካሄደው ድርድር እንደሚሳተፍ በመግለጫው ገልጿል፡
ከዚህ ባለፈም “ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር አፋጣኝና በጋራ ስምምነት ለሚደረግ ተኩስ አቁም ዝግጁ ነኝ” ብሏል ህወሐት በመግለጫው፡፡
ህወሐት በሀገሪቱ ለተከሰተው አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እናምናለንም ብሏል፡፡
በአዲሱ አመት ግጭቱን አቁመን ለሰላም እድል በመስጠት የሰላም እና ብልጽግና መንገድ እንጀምር ያለው ህወሐት፤ “በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ሂደት አስተማማኝ እንዲሆን” እንጠብቃለን ብሏል፡፡
የሰላም ሂደቱ በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ያላቸው ሸምጋዮች እንደሚጨመርና ፤በሂደቱ በሁለቱም ወገኖች መካከል የእርስ በርስ መተማመን እንዲፈጠር የሚያግዙ፣ አፈጻጻምን የሚከታተሉ እንዲሁም አስፈላጊውን መመሪያና ምክር የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንደሚሳተፉም እንደሚፈልግ ህወሓት ገልጿል፡፡፡
በፌደራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የነበረው ጦርነት ለወራት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ በድጋሚ ሊቀሰቀስ ችሏል፤ ጦርነቱን በመጀመር አንደኛቸው ሌላኛቸውን በመክሰስ ላይ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በድጋሚ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛው ቦታ ከህወሓት ጋር እንደሚደራደር መግለጹም ይታወሳል፡፡
ህወሓትም በተመሳሳይ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ቢገልጽም ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ላይ እምነት እንደሌላው ሲገልጽ ቆይቶ ነበር፡፡