የደምበኞቹን ሚስጥር አሳልፎ ሰጥቷል የተባለው ትዊተር 150 ሚልዮን ዶላር ሊቀጣ ነው ተባለ
ትዊተር በፈረንጆቹ 2020 የደምበኞችን ሚስጥር መጠበቅ ባለመቻሉ 400 ሺህ ፓውንድ ተቀጥቶ ነበር
ትዊተር በፈረንጆቹ 2020 የደምበኞችን ሚስጥር መጠበቅ ባለመቻሉ 400 ሺህ ፓውንድ ተቀጥቶ እንደነበር አይዘነጋም
የደምበኞቹም ሚስጥር አሳልፎ ሰጥቷል የተባለው የትዊተር ኩባኒያ 150 ሚልዮን ዶላር ሊቀጣ እንደሚችል የአሜሪካ ህግ አስከባሪዎች አስታወቁ፡፡
የአሜሪካ የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ትዊተር የተስማማባቸውን መመሪያዎች እንደጣሰ በፍርድ ቤት ተረጋግጠዋል፡፡ትዊተር እንደ ስልክ እና የኢሜል አድራሻ የመሳሰሉ የግል መረጃዎች አሳልፎ እንደማይሰጥ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም የገባውን ቃል አለማክበሩ በምርመራ ማረጋገጡንም ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
የአሜሪካ የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን፤ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ዋና ዓላማው ደግሞ የህግ ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ክትትል ማድረግ ነው፡፡
ትዊተር በፈረንጆቹ ከ2013 ጀምሮ የተጠቃሚዎች አካውንት ደህንነትና ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ወይም የአካውነት ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በሚል የደምበኞቹን ስልክ ወይም ኢሜል የሚጠይቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይህም ተጠቃሚዎች የተዘጋ አካውንታቸውን ለመክፈት የይለፍ ቃል በመቀየር የተዘጋ አካውንታቸው ለመክፈት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡
በዚህም "የትዊተር ገቢ ከማሳደጉ በተጨማሪ ከ 140 ሚልዮን በላይ የትዊተር ተጠቃሚዎች ላይ ተጽእኖ መፍጠር ችለዋል" ሲል የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን የፍትህ ክፍል ገልጿል፡፡
የ'ሰኪዩር ቲም' የኮምፒውተር ደህንነት ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር እያን ሬይኖልድስ "ትዊተር የራሱን ጥቅም ለማሳደግ ሲል የደምበኞቹን እምነት ሳያከበር ቀርቷል እንዲሁም ህግ ጥሷል " ብለዋል።
ኩባንያው ደምበኞቹን " ለአካውንታቹ ዋስትና " በሚል የግለሰቦች መረጃ ለሌሎች ተቋምት አሳልፎ ሰጥቷል ሲሉም አክሏል ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፡፡
እያን ፡ሁኔታው ሚያሳየን ነገር ቢኖር ፤ ኩባንያዎች ግለሰቦችን የተለከቱ መረጃወች እንዳላቸው ነው ሲሉም ተናግሯል፡፡የትዊተር ኩባንያ በፈረንጆቹ 2020 የደምበኞችን ሚስጥር መጠበቅ ባለመቻሉ 400 ሺህ ፓውንድ ተቀጥቶ እንደነበር አይዘነጋም፡፡