ኢኮኖሚ
አረብ ኢምሬትስ ከግብጽ እና ጆርዳን ጋር ላደረገችው የኢንዱስትሪ ጥምረት 10 ቢሊዮን ዶላር መደበች
ሶስቱ ሀገራት ትብብሩን ለመመስረት የሚያስችል ስብሰባ አድርገዋል
አረብ ኤምሬትስ፣ግብጽ እና ጆርዳን “ኢንዱስትሪያል ፓርትነርሽፕ” መሰረቱ
አረብ ኢምሬትስ-ግብጽ እና ጆርዳን በጋራ ለመስራት የሚያስችል “የተቀናጅ የኢንዱስትሪ ፓርትነርሽፕ” ጥምረት መስርተዋል፡፡
ሶስቱ ሀገራት ጥምረቱን ለመመስረት የሚያስችል ስብሰባ አድርገዋል፡፡
የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪና የአድቫንስድ ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶ/ር ሱልጣን አል ጃባር ከግብጽና ጆርዳን ጋር የተደረገው የኢንዱስትሪ ጥምረት ለአረብ አለም አዲስ ሞዴል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ጥምረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ መሳተፍ ይችላል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ዶ/ር ሱልጣን አልጃባር እንደተናገሩት በአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሀያን አቅጣጫ ሰጭነት አቢኪው ሆልዲንግስ በፓርትነርሽፑ ለሚፈጠሩ ፕሮጀክቶች የሚውል 10 ቢሊዮን ዶላር ተመድቧል፡፡
በትናንትናው እለት ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ የጆርዳኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር በሽር አል ካሻውነህ እና የግብጹን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ሞስተፋ ማድቦሊን የተቀበሉ ሲሆን በዛሬው እለት የሶስቱ ሀገራት ጥምረት ይፋ ሆኗል፡፡