ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጄክት አፈጻጸም ምን እንማራለን?
ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጄክት አፈጻጸም ምን እንማራለን?
20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት የተያዘለት “ብራካ” የተሰኘው የሀገሪቱ የኑክሌር ኃይል መርሀ-ግብር በአውሮፓውያኑ 2008 በሀሳብ ደረጃ ታቅዶ ከ12 ዓመታት በኋላ በተያዘለት እቅድ መሰረት ሰሞኑን እውን ሆኗል፡፡ የኑክሌር ኃይል ማመንጫው በዓረቡ ዓለም የመጀመሪያው ነው፡፡ ከአራት ዩኒቶቹ አንዱ ኃይል ማመንጨት የጀመረ ሲሆን ማመንጫው ሀገሪቱን ለቀጣዮቹ 60 ዓመታት እንደሚያገለግል ተገልጿል፡፡ ፕሮጄክቱ በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር 5.6 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን በየዓመቱ 21 ሚሊዮን ቶን የካርቦን ልቀትን ይቀንሳል፡፡ ይህም ፕሮጄክቱ ከከባቢ አየር ጋር ተስማሚ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ የመርሀ-ግብሩ ሂደት ከዚህ በታች በሚገኘው ምስል ተዘርዝሯል፡፡