በአረብ ዓለም ለመጀመሪያ ዩኤኢ ጊዜ የኑክሊየር ማብላያ ፍቃድ ሰጠች
በአረብ ዓለም ለመጀመሪያ ዩኤኢ ጊዜ የኑክሊየር ማብላያ ፍቃድ ሰጠች
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች (ዩኤኢ) በራካህ ለሚገኘው የኑክሊየር ጣቢያዋ፤ በአረብ አለም የመጀመሪያ የሆነውን የኑክሊየር ማብላያ ፈቃድ ሰጠች፡፡
20 ቢሊየን ዶላር ወጭ የሆነበት የኑክሊየር ጣቢያው የተገነባው በተለያዩ አካለት ትብብርና በኮሪያ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን መሪነት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የዩኤኢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ ደ/ር አንዋር ቢን ሞሃመድ ጋርጋሽ ኑክሊየር ኃይልን ለሰላም በመጠቀም ዩኤኢ ከአረቡ አለም የመጀመሪያዋ ትሆናለች ብለዋል፡፡
ጋርጋሽ በትዊተር ገፃቸው ትልልቅ እቅዶችን በማቀድ ነው የልማት መሰናክሎችን ማለፍ የሚቻለው ብለዋል፡፡
የብሔራዊ ኑክሊየር ተቆጣጣሪ ለመጀመሪያዎቹ አራት ማብላያዎች ፍቃድ መስጠቱን የዩኤኢ የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ተወካይ ሀማድ አልካቢ ገልጸዋል፡፡
የባራካህ የኑክሊየር ጣቢያ በዩኤኢ ዋና ከተማ ምስራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2017 ለማጠናቀቅ እቅድ የተያዘ ቢሆን በደህንነትና በመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ምክንያት መዘግየቱን ባለስላጣናት ያስረዳሉ፡፡
የአቡዳቢ ባለስልጣናት ባለፈው ጥር እንዳስታወቁት የኑክሊየር ጣቢያው በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር አስታውቀው ነበር፡፡
ካቢ እንዳሉት ከሆነ ባራካህ ሙሉ በሙሉ ሰራ ሲጀምር ለዩኤኢ ልማት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡