ዩኤኢ ሶስት ተጨማሪ የኒዩክለር ኃይል ማመንጫዎችን በማጠናቀቅ ከልቀት ነጻ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት እንደሚያስችላት ተገልጿል
ዩኤኢ ሶስት ተጨማሪ የኒዩክለር ኃይል ማመንጫዎችን በማጠናቀቅ ከልቀት ነጻ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት እንደሚያስችላት ተገልጿል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች(ዩኤኢ) በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የሆነውን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ሥራ በይፋ ማስጀመሯን አስታወቀች፡፡ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሼክ መሐመድ ቢን ራሽድ አለ መክቱም የብራካ ኒዩክለር ኃይል ማመንጫን በይፋ ሥራ አስጀምረዋል፡፡
ይህ የኒዩክለር ሃይል ማመንጫ የኑክሌር ነዳጅ ፓኬጆችን መጫን፣ አጠቃላይ ሙከራ ማድረጋቸው ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡አሁን ሥራ የጀመረው የመጀመሪያው ዩኒት ሲሆን ይህም ኃይል ለማመንጨት እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡
በቀጣይ ተጨማሪ ሦስት የኒዩክለር ኃይል ማመንጫዎችን ለማስጀመር ዕቅድ መያዙ ተገልጿል፡፡ይህም ሀገሪቱ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እንድሁም ከልቀት ነጻ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት ያስችላታል ተብሏል፡፡ ዕቅዱ ሀገሪቱ ከምትፈልገው ኃይል ሩቡን የሚሸፍን እንድሆን ታቅዷል፡፡ሦስቱም አሁን ላይ በግንባታ ላይ መሆናቸው እና ከሀገሪቱ የኃይል ቋት ጋር መገናኘት እንደሚቀራቸው ተዘግቧል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጥቃቅን ነገሮችን በመሰነጣጠቅ እና ወደ ሕዋ ለመድረስ ያደረገችው ጥረት ለዓለም ትልቅ መልዕክት ከመሆኑም በላይ የአረብ ሀገራት ወደ ሳይንሳዊ ሥራዎቻቸው መመለሳቸውን ያመለክታል ተብሏል፡፡ከዚህ ባለፈም ከሌሎች ኃያል ሀገራት ተርታ እንድሰለፉ የሚያደርግና የማይቻል ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡