የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸውን ጨምሮ ለውጭ ሀገር ሰራተኞች ነጻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ጀመረች
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸውን ጨምሮ ለውጭ ሀገር ሰራተኞች ነጻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ ጀመረች፡፡
የአቡ ዳቢ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውም ይሁን የሌላቸው በሀገሪቱ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰራተኞች በነጻ ምርመራ የሚያደርጉበትን ማእከል በማዘጋጀት ምርመራ በማድረግ ላይ ሲሆን ሰራተኞቹ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። የምርመራ ሂደቱ ከመኖሪያ ፈቃድ መኖር እና አለመኖር ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ሲሆን በሀገሪቱ የሚኖሩ የውጭ ሀገራት ሰራተኞች የቫይረሱ ምልክት ከታየባቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በተዘጋጀላቸው ማዕከል በነጻ ምርመራ ያደርጋሉ፡፡ ዓላማው ቫይረሱን መቆጣጠር እና ሁሉም ነዋሪዎች በቂ የጤና እንክብካቤ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ እንደሆነ መንግስት አስታውቋል።