የታክሲ አገልግሎት ሰጪው ተቋም ኡበር ከሰሞኑ ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተገናኘ በተወነጀለበት ክስ ካሳ ለመክፈል ተስማማ
ኡበር ቴክኖሎጂ የተከፈተበትን የክስ ታሪክ ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት በማቀድ ነው ካሳ ለመክፈል የተስማማው፡፡ ለዚህም 4.4 ሚሊየን ዶላር ፈንድ እንደሚያዘጋጅ አሳውቋል፡፡
የድርጅቱ ሰራተኞች በአለቆቻቸው ፆታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል የሚለውን የማጣራት ሂደት ላለፉት ሁለት አመታት ሲከናወን ነበር በዚህም ኡበር 1964 ላይ በአንቀፅ 7/vii የሰፈረውን የሲቪል መብቶች አዋጅ ጥሷል ተብሏል፡፡
ተቋሙም ከጥር 2014 እስከ ሰኔ 2019 ድረስ ፆታዊ ጥቃት ደርሶብናል ለሚሉ ሰዎች ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
ስምምነቱ ሴቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም በስራ ቦታ የሚደርስባቸውን የወሲብ ትንኮሳ በማጋለጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
ኡበር ቴክኖሎጂ መነሻውን አሜሪካ አድርጎ ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡
ምንጭ፡ ሲ-ኔት