ኡጋንዳ ከአይኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን 567 ተዋጊዎች መግደሏን አስታወቀች
ሙሰቨኒ ኡጋንዳውያን ኤዲኤፍ ሊያደርሰው ከሚችለው ጥቃት እነሰዲጠነቀቁ አሳስበዋል
ተስፋ ቆርጠዋል... የመጨረሻ አማራጫቸው እጅ መስጠት ነው" ብለዋል ሙሰቨኒ
ኡጋንዳ ኮንጎ ውስጥ ባደረገችው ወታደራዊ ዘመቻ ከአይኤስ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸውን 567 አባላትን መግደሏን አስታውቃለች።
በአባላቱ ላይ ግድያው የተፈጸመው ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2021 ዘመቻውን ከጀመረችበት ወዲህ መሆኑን ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሰቨኒ ተናግረዋል።
ጸረ- ካምፓላ የሆነው ቡድን መቀመጫውን በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጫካ በማድረግ በኮንጎ ውስጥ እና በኡጋንዳ ላይ ጥቃት ሲፈጽም ቆይቷል።
ድንበር ጥሶ ለመግባት ከኮንጎ ፍቃድ ያገኘው የኡጋንዳ ጦር አላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስ(ኤዲኤፍ) የተሰኘውን ቡድን ካምፕ ለማውደም እና ተዋጊዎቹን ለመግደል እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ተብሏል።
ፕሬዝደንት ሙሰቨኒ በትናንትናው እለት ባሰሙት ንግግር 567 የቡድኑ ተዋጊዎች መገደላቸውን እና 50 የሚሆኑት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት 'ሰብ ማሽን ገን' እና ሮኬቶች ቡድኑ ይዟቸው ከተገኙ 165 መሳሪያዎች መካከል ናቸው።
"ተስፋ ቆርጠዋል... የመጨረሻ አማራጫቸው እጅ መስጠት ነው" ብለዋል ሙሰቨኒ።
ሙሰቨኒ ኡጋንዳውያን ኤዲኤፍ ሊያደርሰው ከሚችለው ጥቃት እነሰዲጠነቀቁ አሳስበዋል።