ዓለም አቀፍ የተፈናቃዮች ሁኔታ
በዓለማችን 108 ሚሊዮን ሰዎች በግዴታ ተፈናቅለዋል ተብሏል
በግዴታ የተፈናቀሉ ሰዎች ለብቻቸው ሀገር ቢሰጣቸው በህዝብ ብዛት 14ኛው ሀገር እንደሚሆኑ ተገልጿል
የመንግስታቱ ድርጅት የ2022 ዓለም ዓቀፍ የተፈናቃዮች ሪፖርትን ይፋ አድርጓል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ከ108 ሚሊየን በላይ ዜጎች በግዴታ ተፈናቅለዋል።
ተገደው ከተፈናቀሉ 108 ሚሊየን በላይ ዜጎች ውስጥ 62 ሚሊዮን ያህሉ በሀገራቸው ተፈናቅለው በመኖር ላይ ናቸው ብሏል የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን።
ግጭት፣ ብጥብጥ፣ ጦርነት እና ሆን ብሎ ዜጎችን ከሚኖሩበት ማፈናቀል ለዜጎቹ መፈናቀል ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።