ሮናልዶ ለሳኡዲው አልናስር እየተጫወተ ሲሆን ሜሲ ለአሜሪካው ኢንተር ሚያሚ ፈርሟል
የአለማችን ድንቅ የእግርኳስ ተጫዋች ማነው? ሜሲ ወይስ ሮናልዶ የሚለው ጥያቄ የእግር ኳስ ቤተሰቡን ለሁለት መክፈል ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል።
አርጀንቲናዊው ኮከብ በኳታር የአለም ዋንጫን ካነሳ በኋላ ንጽጽሩ ረገብ ያለ ይምሰል እንጂ አሁንም አሃዞችን እያጣቀሱ ለምርጫቸው አስረጂ የሚያቀርቡ አልታጡም።
ሮናልዶ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለማንቸስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪፍ 183 ጨዋታዎችን አድርጎ 140 ጎሎችን አስቆጥሯል፤ ሜሲ ደግሞ ለባርሴሎና እና ፓሪስ ሴንት ጀርሜን 163 ጊዜ ተሰልፎ 129 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
በጎል ብዛት ሮናልዶ ይብለጥ እንጂ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ጎል በማስቆጠር ምጣኔ ሜሲ (0 ነጥብ 79) የተሻለ ነው።
በአለም ዋንጫውም ሜሲ 26 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ጎሎችን በማስቆጠር ከሮናልዶ የተሻለ ውጤት አለው፤ ሮናልዶ ለሀገሩ ፖርቹጋል 22 ጨዋታዎችን አድርጎ 8 ጎሎችን ማስቆጠር መቻሉን የጎል ስፖርት ዘገባ ያወሳል።
ከዚህ በታች የሰፈረው የትራንስፈር ማርኬት አሃዛዊ ንጽጽርም ተጫዋቾቹ በአውሮፓ በነበራቸው ቆይታ የተመዘገቡ ብቻ ናቸው።