ራሷን ስታ ልትሰጥም የነበረችው አሜሪካዊቷ ዋናተኛ በአሰልጣኟ አማካኝነት ህይወቷ ተረፈ
በቃሬዛ ከመወሰዷ በፊት ከገንዳው አጠገብ የህክምና እርዳታ ተሰጥቷታል
አሰልጣኟ አልቫሬዝን ለማዳን የተገደደችው ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል
አሜሪካዊቷ አርቲስቲክ ዋናተኛ አኒታ አልቫሬዝ እሮብ እለት በቡዳፔስት በተካሄደው የአለም ሻምፒዮና ላይ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ ራሷን ስታ ወድቃ ነበር።
ራሷ ስታ በወደቀችበት ሰአት አሰልጣኟ አንድሪያ ፉነቴስ ህይወቷን መታደጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
በተመሳሳይ ዋና የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው ስፔናዊት ፉነቴስ፣ አልቫሬዝ ስትሰጥም ካየች በኋላ ወደ ገንዳው ዘላ ገብታለች።
በቃሬዛ ከመወሰዷ በፊት ከገንዳው አጠገብ የህክምና እርዳታ ተሰጥቷታል።
ባለፈው አመት በኦሎምፒክ ውድድር ወቅት ወደ ገንዳው ውስጥ ዘልላ ከገባች እና ከአሜሪካዊቷ የዋና አጋር ሊንዲ ሽሮደር ጋር ወደ ደኅንነት ስትጎትት ፉነቴስ፣ አልቫሬዝን ለማዳን የተገደደችው ለሁለተኛ ጊዜ ነበር።
“አኒታ በጣም የተሻለች ነች፣ እሷ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነች። እውነቱን ለመናገር ጥሩ ፍርሃት ነበር” ሲል ፉነቴስ ረቡዕ ለስፔኑ ጋዜጣ ማርካ ተናግሯል።