በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከባድ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት እነማን ናቸው?
ሰሜን ኮሪያ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ አላት
ስድስት ሀገራት ደግሞ ብልት እስከ ማኮላሸት ድረስ ወንጀለኞችን ይቀጣሉ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከባድ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት እነማን ናቸው?
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ፖፑሌሽን ሪቪው ሪረሮርት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡
ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡
ይህን ተከትሎ ሀገራት የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን ለመከላከል ፈጻሚነታቸው በተረጋገጡ ተከሳሾች ላይ ከባስ ቅጣት መጣል የሚያስችላቸውን ህግ ያዘጋጃሉ።
ጥብቅ ህግ ካላቸው ሀገራት መካከል ሳውዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቸክ ሪፐብሊክ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ፓኪስታን ዋነኞቹ ናቸው።
ሰሜን ኮሪያ ወንጀሉን መፈጸማቸው በተረጋገጡ ጥፋተኛ አስገድዶ ደፋሪዎችን በእሳት አቃጥላ እንድትገድል የሚፈቅድ ህግ አላት።
ከዚህ በተጨማሪም ሳውዲ አረቢያ ጥፋተኛ የሆኑ የአስገድዶ መድፈር ወንጀለኞችን በሰይፍ ስትገድል ደቡብ ኮሪያ፣ ቸክ ሪፐብሊክ፣ ዩክሬን እና አሜሪካ የደፋሪዎች ብልት በኬሚካል አልያም በቀዶ ህክምና እንዲኮላሽ ያደርጋሉ።