አሜሪካ ከተገደለ 23 ዓመት በሞላው ቱፓክ ሻኩር ዙሪያ አዲስ ምርመራ ጀመረች
የዝነኛው ጥቁሩ ራፐር ቱፓክ ግድያ እስካሁን ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል

በቱፓክ ግድያ ዙሪያ እስካሁን ምርመራም ያልተጀመረ ሲሆን የታሰረ ተጠርጣሪ የለም ተብሏል
አሜሪካ ከተገደለ 23 ዓመት በሞላው ቱፓክ ሻኩር ግድያ ዙሪያ አዲስ ምርመራ ጀመረች።
ቱፓክ ሻኩር መነሻውን በአሜሪካዋ ላስቬጋስ ያደረገ ዝነኛ የራፐር ስልተ ምት ሙዚቀኛ ነበር።
ከአሜሪካ አልፎ ዝነኛ ሙዚቀኛ የሆነው ቱፓክ ተገደለ ከተባለ 23ኛ ዓመቱ ላይ ይገኛል።
በፈረንጆቹ 1996 በላስቬጋስ ሄንደርሰን ባለው መኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ እያሽከረከረ እያለ እንደተገደለ የሚታመን ሲሆን ብዙ አድናቂዎቹ እስካሁን መሞቱን እያምኑም ተብሏል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ግድያው ተፈጽሟል ከተባለ ከ23 ዓመታት በኋላ ፖሊስ አዲስ ምርመራ የጀመረ ሲሆን በሄንደርሰን የሚገኘው መኖሪያ ቤቱን እንደፈተሸም አስታውቋል።
በቱፓክ ሻኩር ግድያ ዙሪያ ፖሊስ ምንም አይነት ምርመራ አላካሄደም የተባለ ሲሆን በግድያው ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ ግለሰብም እንደሌለ ተገልጿል።
አዲስ ምርመራ ጀምሯል የተባለው የላስቬጋስ ፖሊስም ለምን ምርመራ እንደጀመረ፣ በቱፓክ መኖሪያ ቤት ውስጥ ምን እንዳገኘ እና ስለቀጣይ እቅዶቼ አልናገርም ብሏል።
ፖሊስ መቋጫው ስላልተገኘው የቱፓክ ሻኩር ግድያ ምርመራውን በአጭር ጊዜ በማካሄድ ምላሽ መስጠት እንደሚፈልግ አስታውቋል።
ከፈረንጆቹ 1991 ጀምሮ የሙዚቃ ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው ቱፓክ በአጭር ጊዜያት ውስጥ ተወዳጅ እና ተጽዕኖ መፍጠር ችሎ ነበር።
ገና በ25 ዓመቱም ከ75 ሚሊዮን በላይ ኮፒዎችን በመሸጥ ዝነኛ ሙዚቀኛ የነበረ ሲሆን የትራፊክ መብራት ይዞት በቆመበት መኪናው ውስጥ በአራት ጥይቶች ተደብድቦ ህይወቱ ማለፉ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።