ኢኮኖሚ
ከዶላር አንጻር ደካማ ገንዘብ ያላቸው 10 የዓለም ሀገራት
የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለቀወ ዋጋ ጥንካሬውንና ድክመቱን ያሳያል
የኢራን ሪያል፣ የቬትናም ዶንግ እና የሴራሊዮን ሊዮን ቀዳውን ሶስት ደረጃዎች ይዘዋል
የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለው ዋጋ ጥንካሬውን እን ድክመቱን ያሳያል የተባለ ሲሆን፤ ኤፍ.ኤክስ.ኤስ.ኤስ.አይ ድረ ገጽ ከሰሞኑ ከከዶላር አንጻር ገንዘባቸው ደካማ የሆነ 10 የዓለም ሀገራትን ይፋ አድርጓል።
ከዓለም ከዶላር አንጻር ደካማ ገንዘብ ያላት ቀዳሚ ሀገር ኢራን ነች የተባለ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ42 ሺህ 45 የሀገሪቱ ገንዘብ (ሪያል) ይመነዘራል።
የቬትናም ገንዘብም ከዶላር አንጻር ደካማ ከሚባሉት ውስጥ 2ኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ24 ሺህ 469 የቬትናም ገንዘብ (ዶንግ) ይመነዘራል።