ሊባኖስ 1 የአሜሪካ ዶላር በ15 ሺህ የሀገሪቱ ፓውንድ እንዲመነዘር ወሰነች
ሊባኖስ የገንዛቧን የመግዛት አቅም ከዶላር አንጻር በ90 በመቶ ማዳከሟን የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል
በሊባኖስ ከዚህ በፊት አንድ ዶላር በ1500 የሀገሪቱ ፓውንድ ይመነዘር ነበር
ሊባኖስ ከዶላር አንጻር የገንዘቧን የመግዛት አቅም ይበልጥ ማዳከሟ ተነገረ።
የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የሊባኖስ ፓውድ ከዶላር አንጻ የመግዛት አቅሙ በ90 በመቶ እንዲዳከም መወሰኑንም ነው ያስታወቀው።
ከውሳኔው በፊት አአንድ የአሜሪካ ዶላር በ1 ሺህ 500 የሊባኖስ ፓውንድ ይመነዘር የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ ግን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ15000 የሊባኖስ ፓውንድ እንዲመነዘር መወሰኑን ይፋ አድርጓል።
ሊባኖስ የሀገሪቱን ፓውንድ የመግዛት አቅም ስታዳከም ከ25 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፤ የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክም የአንድ የአሜሪካ ዶላር ይፋዊ የምንዛሬ ዋጋ 15 ሺህ ፓውንድ መሆኑን ትናንት አረጋግጧል።
የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ ይህንን ይበል እንጂ በትይዩ ወይም በጥቁር ገበያው ግን አንድ ዶላር እስከ 60 ሺህ የሊባኖስ ፓውንድ እንደሚመነዘር ተዘግቧል።
የሊባኖስ ፓውንድ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከፍተኛ ውድቀት እንዳጋጠመው የሚታወቅ ሲሆን፤ ፣ በርካታ ሊባሳውያን ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግርን ለዚህ እንደ መንስዔነት ያሳሉ።
ሊባኖስ የገንዘቧን የመግዛት አቅም ያዳከመችው እና ከትይዩ ገበያ ጋር ለማቀራረብ ያደረገችውወ ውሳኔ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የ3 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ፓኬጅ ለማግኘት እና ኢኮኖሚዋን ከውድቀት ለመውጣት የሚረዳ ነው ተብሏል።